Saturday, 09 January 2021 12:22

“ቅን ፍላጎት እስካለ መንገድ አለ” መፅሐፉ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ አንዳርጋቸው አሰግድ የተፃፈውና በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታዎች ዙሪያ የሚያጠነጥነው “ቅን ፍላጎት እስካለ መንገድ አለ” መፅሐፍ ለንባብ በቅቷል።
መፅሐፉ በዋናነት በሀገሪቱ እየታየ ያለው የሽግግር ጊዜ ፈጣን ውሳኔና አመራር ስለመሻቱ፣ አገርን ወደፊት ለማስቀጠል ስለ የጋራ ራዕይ አስፈላጊነት፣ የኢትዮጵያ የብሔሮች ጥያቄ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሄደ፣ ከጡንቻ ፖለቲካ በአማራጭ ፖለቲካ እንዴት መብለጥ እንደሚቻልና በአጠቃላይ በፖለቲካ አመራሮችም ሆነ በተቃውሞ ጎራው ባሉት በኩል ቅን ፍላጎት እስካለ ድረስ ብሩህ መንገድ እንዳለ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በ215 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ120 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን “እነሆ” መፃሕፍት መደብር በዋናነት እያከፋፈለው ይገኛል። ደራሲው ከዚህ ቀደም “በአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም።


Read 11447 times