Saturday, 09 January 2021 11:10

ኢዜማ ጠበቅ ያለ የምርጫ ሥነ ምግባር ደንብ አወጣ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

    ደንቡን ጥሶ የተገኘ በፍ/ቤት ክስ ሊመሰረትበት ይችላል
                 
              ኢዜማ አመራሮቹና አባላቱ በቀጣዩ ምርጫ የሚተዳደሩበትን  የስነ ምግባር ደንብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ደንቡን የማያከብሩ እስከ ፍ/ቤት ድረስ ክስ ሊቀርብባቸው ይችላል ብሏል፡፡
16 ያህል ዋና ዋና የስነ ምግባር መመሪያዎችን የደነገገው የኢዜማ የምርጫ  ስነ ምግባር ደንብ፣ ከታህሳስ 9 ቀን 2013 ጀምሮ በተግባር የዋለ ሲሆን ደንቡ ቀጣዩን ምርጫ በሃቅ ላይ የተመሰረተ በማድረግ  ፓርቲው የድርሻውን ለመወጣት ያዘጋጀው መሆኑም ተገልጿል፡፡
 ኢዜማ ቀጣዩ ምርጫ ለውጥ የሚያመጣ ነው የሚል እምነት  መሰነቁን ለአዲስ አድማስ ያስረዱት የፖለቲካ  የምርጫ ስትራቴጂና ማኔጅመንት ሃላፊ ወ/ሮ ከውሰር ኢንድሪስ፤ የስነ - ምግባር ደንቡ አባላት ሃላፊነትና ግዴታቸውን አውቀው በልካቸው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስገድድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ምርጫው እንከን የለሽ ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም እንኳ በሚፈለገው መጠን የተሻለ ምርጫ ይካሄዳል የሚል እምነት የያዘው ኢዜማ፤  በዚህ ምርጫ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠውን ፓርቲ እውቅና ሰጥቶ ሃገሪቱን ከገባችበት ውስብስብ ችግር ማሻገር ያስፈልጋል የሚል ግምገማ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡
ይህን የስነ ግባር ደንብ የጣሰ የኢዜማ አመራር ወይም አባል፣ በመጀመሪያ በተደራጀበት ወረዳ በተቋቋመው ሶስት አባላት ባሉት የህግና  ስነ ስርአት ኮሚቴ ጉዳዩ ታይቶ እርምት እንዲወስድ ያደረጋል፤ በዚህ የማይቋጭ ከሆነ ለኢዜማ ብሄራዊ ዲስፒሊን ኮሚቴ ይቀርባል፤ ከዚህም ካለፈ በሀገሪቱ ህግ በፍ/ቤት ይቀርባል፤ ከዚያም እንዲጠየቅ ጭምር ይደረጋል ብለዋል - ሀላፊው ፓርቲው ተፎካካሪ ድርጅቶች በየትኛውም የሃገሪቱ አካባቢ ያለገደብ መንቀሳቀስ መቻል፣ መራጩ ህዝብ ሳይፈራ በነጻነት የፈለገውን ተፎካካሪ የሚመርጥበት ሃገራዊ ድባብ መኖር፣ ከምርጫው ጋር ግንኙነት ያላቸው የምርጫ ቦርድን ጨምሮ የፌደራሊዝም ሆነ የክልል መንግስት ተቋማት ተፎካካሪዎችን በእኩልነት ማስተናገድና የህዝብ ድምጽ በአግባቡና በታማኝነት መቆጣጠር መቻልቻል ምርጫውን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ዋና ዋና መመዘኛዎች መሆናቸውን ኢዜማ ጠቁሟል።
ከኢዜማ ዋና አመራሮች እስከ አባላትና ደጋፊዎች ድረስ ወርዶ ይተገበራል የተባለው የኢዜማ የምርጫ 2013 የስነ ምግባር ደንብን    አባላቱም ሆኑ ደጋፊዎች በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተረጋገጠ የመጨረሻ የምርጫ ውጤት ተገዢ እንደሆኑ ወይም እንዲቀበሉ፤ ፓርቲውም ውጤቱን እንደሚቀበል ያመለክታል፡፡ በምርጫው ላይ አባላቱም ሆኑ ደጋፊዎቹ የሚኖራቸውን ቅሬታ በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲያቀርቡ እንዲሁም የሃገሪቱን  የምርጫ ደንቦችና ስነ-ምግባሮች በሙሉ እንዲያከብሩ ያስገድዳል -የስነ ምግባር ደንቡ ለኢዜማ አባላት በምርጫ 2013 ወቅት ሚዲያዎችን አባሎች ማንጓጠጥ፣ መስራቸውን እንዳያከናውኑ እንቅፋት መሆን፣ ሌሎች ፓርቲዎችን፣ ማወክና፣ ፍርሃት እንዲሰማቸው ወይም ንብረታቸው እንዲጎዳ ማድረግ፣ ስብበሰባቸውና ሰላማዊ ሰልፋቸው ማወክ፣ መገደብ እንቅፋት መሆን ፈጽሞ የተከለከለ ነው ይላል - ደን፡፡
በምርጫው ሂደትም ኢዜማ መራጮች ያለ ምንም እንቅፋት ምርጫውን እንዲያከናውኑ በምርጫ አስፈፃሚዎች ተገቢውን ክብር መስጠት እንዲሁም የምርጫው ሚስጢራዊነት እንዲጠበቅ ኢዜማና አባላቱ ያደርጋሉ ብሏል፡፡
በምርጫው  ወቅትም በቋንቋ አጠቃቀም ረገድ ሃላፊነት ክብርን ባረጋገጠ ደረጃ አባላቱ ቋንቋ መጠቀም እንደሚኖረውባቸው የሚያስገድደው ደንቡ፣ ግጭት የሚያነሳሱ፣ የሚያንቋሽሹ፣ የሚያስፈራሩ፣ በማናቸውም መልኩ በየትኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ መፈጸም ክልክል ነው፤ እንዲሁም የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች ግጭት ቀስቃሽ ቃላቶችንም ሆነ ጽሁፎችን በማናቸውም መንገድ በግልፅም በስውር ማስተላለፍና ማሰራጨት ፈጽሞ የተከለከለለ ነው ይላል ደንቡ፡፡
በምርጫ ወቅት የምልክት አጠቃቀምን በተመለከተም የሌሎችን ፓርቲዎች ምልክት አስመስሎ መጠቀም፣ የሌሎችን ማበላሸትና ማጥፋት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን የሚደነግገው ደንቡ፤ በሌሎች ላይ የማዋከብ፣ጸበኝነትና አምባጓሮ የመፍጠር ሁኔታዎች ፈፅሞ የተከለከለ ነው ብሏል፡፡
ሙስናና ጉቦ ወይም ሌሎችን በገንዘብ ለመደለል መሞከር በኢዜማ የሚፈቀድ አለመሆኑንም የስነ- ምግባር ደንቡ ይደነግጋል፡፡  

Read 11918 times