Saturday, 11 August 2012 09:51

የህክምና ትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቅ ፕሮጀክት ሊተገበር ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

የህክምና ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የህክምና ባለሙያዎችን ፍልሰት ለመቀነስ ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆነው ከሰሀራ በታች ከሚገኙ 12 አገራት ከተውጣጡ 33 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳድሮ ነው፡፡ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የጤናውን ዘርፍ ለማስፋፋትና ጥራቱን ለማስጠበቅ አሜሪካ የምትከተለው ስትራቴጂ አካል የሆነው የሜዲካል ፓርትነርሺፕ ኢንሺዬቴቭ (ሜፒ) ሁለተኛ አመታዊ ጉባዔውን ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባካሄደበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ከሰሀራ በታች ከሚገኙ 12 አገራት የተውጣጡ 33 ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለመሆን የተወዳደሩ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረጡት 13 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኗል፡፡

የሜፒ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ሚሊያርድ ደርበው እንደተናገሩት፤ የፕሮጀክቱ ዓላማ የህክምና ጥራትን በማሻሻል፣ በእውቀትና በሥነ ምግባር የታነፁና ብቃት ያላቸው የህክምና ባለሙያዎችን ማፍራት ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች ፍልሰትን ለመቀነስም በተለያዩ መንገዶች እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡ የህክምና ተማሪዎችም በኢለርኒንግ ሲስተም (በኢንተርኔት የማስተማር ዘዴ) ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ከፕሮጀክቱ ዓላማዎች አንዱ ሲሆን ይህም በቀጣዩ አዲስ አመት መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ዶ/ር ሚሊያርድ ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ዩኒቨርሲቲዎች የአስር ሚሊዮን ብር እርዳታም እንደሚያገኙ በጉባዔው ላይ ተገልጿል፡፡

 

 

Read 15354 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 14:52