Wednesday, 09 December 2020 00:00

ለጎብኝዎች እጅግ አደገኛ የሆኑ የአለማችን አገራት ይፋ ተደረጉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  ኢንተርናሽናል ኤስኦኤስ የተባለው ተቋም በ2021 የፈረንጆች አመት ለጎብኝዎችና መንገደኞች እጅግ አደገኛ የሆኑና ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ይኖርባቸዋል ያላቸውን የአለማችን አገራት ዝርዝር ከሰሞኑ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ሊቢያ፣ ሶርያና አፍጋኒስታን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
የፖለቲካ ነውጥ፣ ማህበራዊ አለመረጋጋት፣ የደህንነት ሁኔታ፣ የአደጋ ጊዜ ምላሽ አገልግሎቶች ሁኔታ እና የወንጀል ድርጊቶችን ጨምሮ በተለያዩ የደህንነት ስጋት መመዘኛዎች ተጠቅሞ በመገምገም፣ የአለማችን አገራትን የአመቱ የስጋት ደረጃ ይፋ ያደረገው ተቋሙ፣ ኢራቅና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የአራተኛና አምስተኛ ደረጃ መያዛቸውንም አመልክቷል፡፡
በአመቱ እጅግ አነስተኛ የስጋት ደረጃ ይኖራቸዋል ተብለው በሪፖርቱ የተጠቀሱት ሰባት የአለማችን አገራት በሙሉ የአውሮፓ አገራት ሲሆኑ፣ አይስላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ ስሎቫኒያና ሉግዘምበርግ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተጓዦች መይም መንገደኞች ላይ እጅግ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረባቸው ሶስቱ የአለማችን አገራት ብሎ ተቋሙ የጠቀሳቸው አገራት ሩስያ፣ ዩክሬንና ኦስትሪያ ሲሆኑ፤ በአንጻሩ አነስተኛ ተጽዕኖ ያደረሰባቸው ያላቸው አገራት ደግሞ ኒውዚላንድ፣ ታንዛኒያና ኒካራጓ ናቸው፡፡


Read 1272 times