Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 04 August 2012 12:49

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምኞት እና አድናቆት

Written by 
Rate this item
(44 votes)

የኦሎምፒክ መድረክ ለወከሉን ኦሎምፒያኖች ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻቸውም የኩራትና የአድናቆት ምንጭ እንደሆነ ለስፖርት አድማስ አስተያየታቸውንና መልካም ምኞታቸውን የገለፁት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ የሚመዘገብ አመርቂ ውጤት ደስታው የአትሌቶቻችን ብቻ አይደለም ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ  እስከዛሬ ከተገኘው የበለጠ የሜዳሊያ ብዛት፣ በወርቅ፣ ብር እና ነሐስ አዲስ ከተሳተፉት አትሌቶቻችን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡ ብዙዎቹ አስተያየት ሰጪዎች  3 እና 4 የወርቅ ፣ 2 የብር እና የ3 ነሐስ ሜዳልያዎችን ተመኝተዋል፡፡  የከተማው ነዋሪዎች ታላቁ የስፖርት መድረክ እድሜ ፤ ፆታ እና ዘር ሳይለዩ በአንድ ላይ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው ሲገልፁ በኦሎምፒክ ሰሞን በአትሌቶች የሚገኝ ስኬት ኢትዮጵያ በድህነቷ ብቻ የምትጠራበትን አሰልቺ ሁኔታ ይቀይራል ሲሉ ኦሎምፒክ አገራችንን ከሌሎች አለም አገራት ጋር የሚያገናኝና የሚያስተዋውቅ በመሆኑ እንደሰትበታለን ብለዋል፡፡

የስፖርት አድማስ ተባባሪ ሪፖርተር የሆነችው ግሩም ተሰማ  በካዛንቺስ፤ በአራት ኪሎ፤ በፒያሳ፤ በአዲሱ ገበያ እና በሌሎች የአዲስ አበባ ስፍራዎች ያነጋገረቻቸው አስተያየት ሰጭዎች  በእነ አበበ ቢቂላ ፈርቀዳጅነት የተጀመረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ገድልና ጀግንነት ኩራታቸው ነው፡፡ የአትሌቶቻችን ጀግንነት  በኦሎምፒክ ሰሞን ብቻ ሳይሆን በማናቸውም አጋጣሚዎቻቸው የሚያስታውሷቸው የማይረሷቸው ትዝታዎቻቸው መሆናቸውን ሲጠቅሱም በተለይ ከአሁኑ ዘመን ኦሎምፒያኖች ለኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ቀነኒሣ በቀለ እና ጥሩነሽ ዲባባ የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡  በ4 ኦሎምፒኮች ያልተደፈረው የ10ሺ የወርቅ ክብር ትናንት ምሽት ዓለም በከፍተኛ ጉጉት የጠበቀው የሴቶች 10ሺ ሜትር ተካሂዷል፡፡ የተወዳደሩት ኢትዮጵያውያን ኦሎምፒያኖች ጥሩነሽ ዲባባ ፤ ወርቅነሽ ኪዳኔና በላይነሽ ኦልጅራ ሲሆኖ ውጤታማነታቸው በቀጣይ ውድድሮች ኢትዮጵያ ለሚኖራት ስኬት መነቃቃት እንደሚፈጥር ታምኖበታል፡፡ ውድድሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ሊስብ የቻለው በኢትዮጵያዋ ጥሩነሽ ዲባባ እና በኬንያዋ ቪቪያን ቼሮይት መካከል ከባድ ትንቅንቅ እንደሚታይበት በመጠበቁ ነበር፡፡ በአቴንስ  እና ቤጂንግ ኦሎምፒኮች በ10ሺ ሜትር ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ያላት ጥሩነሽ ዲባባ በትናንቱ ውድድር ሻምፒዮናነቷን ስታስጠበቅ በ3  ኦሎምፒኮች 3 የወርቅ ሜዳልያ  ያገኘች ብቸኛ አትሌት ትሆናለች፡፡ ባለፈው ዓመት ጥሩነሽ በጉዳት ከውድድር በመራቋ  የኬንያዋ አትሌት ቪቪያን ቼሮይት ገንናለች፡፡ በኮርያ ዳጉ በተደረገው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10ሺ እና 5ሺ ሜትር ውድድሮች ድርብ የወርቅ ሜዳልያ ድሎችን በማስመዝገቧም በሁለቱም ርቀቶች በለንደን ኦሎምፒክ ከፍተኛ ግምት እንድታገኝ ምክንያት ሆኗል፡፡ በትራክ ላይ የ10ሺ እና 5ሺ ሜትር 11 ውድድሮች ሁለቱ አትሌቶች ሲገናኙ ሁሉንም ያሸነፈችው ጥሩነሽ ዲባባ ነበረች፡፡ ቀነኒሳ የወርቅ ሜዳልያ ሃትሪክ፤ የወንድማማቾቹ ፍጥጫ እና የሞ ፋራህ ፉከራዛሬ ምሽት ላይ በ10ሺ ሜትር ወንዶች ሌላው ወሳፅ ፍልሚያ ይደረጋል፡፡ ከ1996 የአትላንታ ኦሎምፒክ ጀምሮ 4 የወርቅ ሜዳልያዎችን ሁለቱን በኃይሌ አትላንታ እና ሲድኒ ላይ እንዲሁም ሁለቱን በቀነኒሳ አቴንስ እና ቤጂንግ ላይ ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ በለንደን ይሄው ስኬት ተደግሞ በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ በታሪክ 6ኛውን በተከታታይ 5 ኦሎምፒኮች 5ኛውን የወርቅ ሜዳልያ መገኘቱ ይጠበቃል፡፡ በ10ሺ ሜትር ውድድሩ ኢትዮጵያን ከወከሉት ኦሎምፒያኖች ከፍተኛው ግምት የተሰጠው በርቀቱ 2 የኦሎምፒክና 5 የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያዎችን የሰበሰበው እና የርቀቱን የዓለም እና የኦሎምፒክ ሪከርድ የያዘው የ30 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ ነው፡፡ ከቀነኒሳ ጋር በአስቸጋሪው የ10ሺ ሜትር ውድድር ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ የሚያደርገው ፉክክር ይጠበቃል፡፡ በሜዳልያ ተፎካካሪነት ከኢትዮጵያውያኑ ኦሎምፒያኖች ጋር ስሙ ሊጠቀስ የበቃው ደግሞ እንግሊዝን የሚወክለው ሞፋራህ ብቻ ነው፡፡ በ1968 እኤአ ላይ ሜክሲኮ ኦሎምፒክ ላይ በርቀቱ ብቸኛ የወርቅ ሜዳልያ ያገኘችው  ኬንያ ብዙም አልተገመተችም፡፡ በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በ10ሺ ሜትር ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች በ5ሺ ደግሞ 1 የወርቅ እና 1 የብር ሜዳልያ በማግኘት ከፍተኛውን ውጤት የያዘው ቀነኒሳ በቀለ በዛሬው የ10ሺ ሜትር ውድድሩ በድጋሚ ካሸነፈ የነበረውን የውጤት ክብረወሰኑን ያሻሽላል፡፡ ኃይሌ ገብረስላሴ ሰሞኑን በሰጠው አስተያየት በ10ሺ ሜትር ውድድሩ የወርቅ ሜዳልያው ድል ለቀነኒሳ እንደሚያጋድል መስክሯል፡፡ በውድደሩ የሚኖረው የአሯሯጥ ሁኔታ የፈጠነ ከሆነ ለቀነኒሳ ማሸነፍ ምክንያት እንደሚሆን የገለፀው ኃይሌ ሩጫው ዝግ የሚል ከሆነ  ለእንግሊዛዊው ሞ ፋራህ የማሸነፍ እድል ሊፈጠር እንደሚችል ገምቷል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺ ሜትር ውድድሩ ለማሸነፍ ስላለው ፍላጎት ለጋርድያን ሲገልፅ‹ ታሪክ በልቤ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ በ3 ኦሎምፒኮች 3 የወርቅ ሜዳልያ ለማሳካት መቻል ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሳስብበት ቆይቻለሁ፡፡ የሚሳካልኝ ከሆነ በእውነት ትልቅ ክብር ነው ›ብሏል፡፡እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ባለፈው አመት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ውድድሮች ድርብ የወርቅ ሜዳልያዎችን ወስዷል፡፡  በርቀቱ የእንግሊዝና የአውሮፓ ሪከርዶችን ዘንድሮ ያስመዘገበው  ሞ ፋራህ ስለውድድሩ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ወቅታዊ ብቃቱ  በፈጠረለት የመተማመን ስሜት ለሜዳልያ ድል እንደሚያበቃው ተናግሯል፡፡ ሞ ፋራህ ስለ ቀነኒሳ ተምሳሌትነትም የገለፀው ነገር አለ፡፡ ቀነኒሳ  በአዋቂ ውድድሮች በፍፁም የበላይነት እያሸነፈ በነበረበት ወቅት እኔ በወጣት ውድድሮች ነበርኩ ያለው ሞ ፋራህ ዛሬ በኦሎምፒክ ስንገናኝ ለስፖርቱ ያደረገውን ታላቅ የስኬታማነት አስተዋፅኦ በአርዓያነት እየተመለከትኩ ነው ብሏል፡፡ማራቶን ልእልቷ ትመለስ ይሆን ወደ ቤቷኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ በሴቶች ማራቶን ከፍተኛውን ውጤት ከ16 ዓመታት በፊት በአትላንታ ኦሎምፒክ በፋጡማ ሮባ የወርቅ ሜዳልያ ድል ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ  ነገ በሚካሄደው የሴቶች ማራቶን ይህን ታላቅ ክብር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው ሶስቱ ወጣት ኦሎምፒያኖች የ25 አመቷ ቲኪ ገላና፤ የ26 ዓመቷ አሰለፈች መርጊያ እና የ22 አመቷ ማሬ ዲባባ ናቸው፡፡ ዘንድሮ የሮተርዳም ማራቶንን ያሸነፈችው ቲኪ ገላና በዓለም የማራቶን  ፈጣን ሰዓት 2ኛ ያለውን 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ 58 ሰኮንዶች ያስመዘገበች  በዱባይ ማራቶን 1 እኛ እና ሁለተኛ የወጡት እና በዓመቱ የፈጣን ሰዓት ደረጃ በ4ኛ እና በ6ኛ ደረጃ ላይ የተመዘገቡ ሰዓቶች ያሏቸው አሰለፈች መርጊያ እና ማሬ ዲባባ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ናቸው፡፡ አምና በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን የነሐስ ሜዳልያ ያገኘችው እና በፓሪስ እና የዱባይ ማራቶን ውድድሮች ከፍተኛ ልምድ ያላት አሰለፈች መርጊያ  ሰዓቷ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ1 ሰኮንዶች ነው፡፡ ማሬ ዲባባ በበኩሏ በርቀቱ ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓቷ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ52 ሰኮንዶች ነው፡፡ከ4 ዓመት በፊት በቤጂንግ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን በፀጋዬ ከበደ የተገኘው የነሐስ ሜዳልያ ዘንድሮ በተሻለ ውጤት መደገሙ የሚያጠያይቅ ይመስላል፡፡ዋናው ምክያት ደግሞ በውድድሩ ለሚቀርቡ ሜዳልያዎች ዋንኛዎቹ ተፎካካሪዎች የኬንያ ምርጥ አትሌቶች መሆናቸው በስፋት መገለፁ ነው፡፡ በኦሎምፒኩ የመጨረሻ ቀን ዋዜማ ላይ በሚደረገው የወንዶች ማራቶን  አየለ አብሽሮ፤ ዲኖ ሰፈር እና ጌቱ ፈለቀ ተሳታፊ ናቸው፡፡ ዘንድሮ የዱባይ ማራቶንን ሲያሸንፍ በማራቶን የምንገዜም 4ኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው አየለ አብሽሮ በሜዳልያው ትንቅንቅ ሊገባ እንደሚችል ግምት አለ፡፡ ቤጂንግ ኦሎምፒክ ለኬንያ በታሪክ የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘውን ሳሙኤል ዋንጂሩ ታሪክ ለንደን ላይ ለመድገም ከፍተኛ ግምት ያገኘው ያለፉትን ሁለት የለንደን ማራቶን ውድድሮች ያሸነፈው የ30 ዓመቱ ኬንያዊ ዊልሰን ኪፕሶንግ ነው፡፡ የሁለት ግዚያት የማራቶን የዓለም ሻምፒዮኑ አቤል ኪሪዊምም ይጠበቃል፡፡አስጨናቂው 5ሺ ከ4 ዓመት በፊት በ29ኛው ኦሎምፒያድ ቤጂንግ ላይ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ውድድሮች ድርብ የወርቅ ሜዳልያዎችን ለማስመዝገብ የቻሉት ሁለቱ የኢትዮጵያ ምርጥ ኦሎምፒያኖች ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ  በለንደን ኦሎምፒክ ይህን ታሪካዊ ድላቸውን ለመድገም ይጠበቁ ነበር፡፡ ሁለቱ አትሌቶች ተሸንፈው በማያውቁበት የ10ሺ ሜትር ውድድር ትናንት እና ዛሬ በቋሚ ተሰላፊነት ኦሎምፒኩን ቢካፈሉም በ5ሺ ሜትር ተጠባባቂ መሆናቸው ስፖርት አፍቃሪውን ሲያስጨንቅ የሰነበተ ነው በኦሎምፒክ ልኡካን ደንብ መሰረት በየተኛውም ርቀት በተጠባባቂነት የተያዙ አትሌቶች ወደ ኦሎምፒኩ መካሄጃ ከተማ የሚሄዱ ባይሆንም በ10ሺ ሜትር ቋሚ ተሳላፊ የሆኑት ቀነኒሳ ጥሩነሽ በለንደን ይገኛሉ፡፡ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪኳ አቴንስ ላይ በ2004 እኤአ ላይ የነሐስ እንዲሁም ከ4 ዓመት በፊት በቤጂንግ የወርቅ ሜዳልያ የወሰደችና የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን ከያዘች 5 አመታት ያለፋት አትሌት ናት፡፡ በሴቶች 5ሺ ሜትር ኢትዮጵያን በመወከል የሚሮጡት ሶስቱ ኦሎምፒያኖች በ2004 እኤአ አቴንስ ላይ የመጀመርያውን የኢትዮጵያ 5ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ በሴቶች ያስገኘችው መሰረት ደፋር፤ በ1500 ሜትር የዓለም ኢንዶር ሻምፒዮን የሆነችው ገለቴ ቡርቃ እና ወጣቷ እና በኦሎምፒክ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ የምትሰለፈው ገነት ያለው ናቸው፡፡ የቋሚ ተሰላፊዎቹ ምርጫ  ሰዓትን የተንተራሰ ሲሆን ሶስቱ አትሌቶች በሮም ዳይመንድ ሊግ ውድድር ከ1 እሰከ 3 ሲወጡት የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች በማስመዝገባቸው ነው፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ ዘንድሮ በ5ሺ ሜትር አንድ ውድድር በኒውዮርክ ዳይመንድ ሊግ አድርጋ ስታሸንፍ ያስመዘገበችው ሰዓት በአመቱ ለኢትዮጵያውን አትሌቶች 4ኛው ፈጣን ሰዓት ስለነበር በተጠባባቂነት ተይዛለች፡፡በወንዶች 5ሺ ሜትር የተያዙት በኦሎምፒክ መድረክ የመጀመርያ ተሳትፎ የሚያደርጉት እና በውድድር ዘመኑ በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ምርጥ ብቃት ይዘው የሚገኙት ሶስት አትሌቶች ናቸው፡፡ ሶስቱ አትሌቶች  የዘንድሮውን ዳይመንድ ሊግ የሚመራው ደጀን ገብረመስቀል፤ በሀለተኛ ደረጃ የሚገኘው ሐጎስ ገብረ ህይወት እና የኔው አላምረው ናቸው፡፡ አትሌቶቹ በ5ሺ ሜትር ቋሚ ተሰላፊ ሆነው ሊመረጡ የበቁት በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ከ1 እሰከ 3 ተከታትለው ሲገቡ ከ12.50 ደቂቃዎች በታች  በመግባት የመጀመርያዎቹን ሶስት የኢትዮጵያ የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች በማስመዝገባቸው ነው፡፡ በ5ሺ ሜትር የዓለም እና የኦሎምፒክ ሪከርዶችንና የሻምፒዮናነት ክብሮች የያዘው አትሌት ቀነኒሳ በበኩሉ በርቀቱ በኢትዮጵያ የዓመቱ 5ኛው ፈጣን ሰዓትን ማስመዝገቡ

 

ጠባባቂ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ የሴቶች 5ሺ  የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ማክሰኞ ይደረግና የሜዳልያው ፍልሚያ የነገ ሳምንት ይሆናል፡ በ5ሺ ሜትር ወንዶች የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ረቡእ ተደርጎ የሜዳልያ ትንቅንቁ በመቀጠል በሚመጣው ሰኞ ይሆናል፡፡ በመካከለኛ ርቀቶች በ800፤ በ1500ሜ እና በ3ሺ መሰናክልበ30ኛው ኦሎምፒያድ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ልዩ ያደረጉት በሜዳልያ ተስፋ የገቡ ኦሎምንፒያኖች የሚካፈሉባቸው የመካከለኛ ርቀት የአትሌቲክስ ውድድሮች ናቸው፡፡ በተለያዩ ሁኔታዎች በመካከለኛ ርቀት በተሰሩ የሜዳልያ ትንበያዎችና ግምቶች የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ እድል ያልተጠበቀ ሲሆን የብርና የነሐስ ሜዳልያ ድሎች ግን በ1500 ሴቶች፤ በ3ሺ መሰናክል ሴቶች እና በ800 ሜትር ወንዶች ግምት ተሰጥቷል፡፡ በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ሚኒማውን አሟልተው ለመሰለፍ የሚበቁት የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በሴቶች ፋንቱ ሚጌሶ እና በወንዶች መሃመድ አማን ናቸው፡፡ በወንዶች 800 ሜትር የኢትዮጵያን ሪከርድ የያዘው መሃመድ አማን  ለወርቅ ሜዳልያ ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን የኬንያ አትሌት ዴቪድ ሩዲሻ ለመቀናቀን ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ከአመት በፊት ከ35 ውድድሮች ያለመሸነፍ ቆይታ በኋላ ዴቪድ ሩዲሻ የተሸነፈው በመሃመድ አማን ነበር፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ ለዴቪድ ሩዲሻ እና ለመሃመድ አማን ፉክክር ትኩረቱ ቢያመዝንም የሱዳኑ አቡበከር ካኪም በተፎካካሪነት ይጠቀሳል፡፡ በሴቶች 800 ሜትር አዲስ ታሪክ ለኢትዮጵያ እንደምትሰራ ከፍተኛ እምነት ያሳደረችው ፋንቱ ሚጌሶ በሜዳልያ ፉክክሩ ለመግባት ከባድ ፈተና የሚጠብቃት ይመስላል፡፡ በርቀቱ የኦሎምፒክ ሻምፒዮናዋ ኬንያዊት ፓሜላ ጄሊሞ፤ የዓለም ሻምፒዮናዋ ራሽያዊት ማርያ ሳቪኖቫ፤ የአሜሪካዋ አሊሽያ ሙንቶኖ እና የደቡብ አፍሪካዋ ካስተር ሴማንያ የሜዳልያ እድላቸው በስፋት ግምት ያገኘ ነው፡፡በ800 ሜትር የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ሰኞ ከተካሄደ በኋላ ግማሽ ፍፃሜው በማግስቱ ተደርጎ የሜዳልያ ትንቅንቁ ሀሙስ ይወሰናል፡፡ በተመሳሳይ ርቀት በሴቶች ምድብ የመጀመርያ ዙር በመጭው አርብ ተደርጎ ግማሽ ፍፃሜው የዛሬ ሳምንት ይደረግና ፍፃሜው ከ2 ቀናት በኋላ ነው፡፡በ1500ሜ ትር ከፍተኛ የሜዳልያ ተስፋ ሊኖራት የሚችለው በሴቶች ምድብ ቢሆንም ያመቱን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሞሮካዊ አትሌት ማድያም ሲሊቫሊ ለወርቅ ሜዳልያው ዋና ተቀናቃኝ ተደርጋለች፡፡ በውድድር ዘመኑ ከየትኛው አትሌት በላቀ ብዙ ውድድሮች ያሸነፈችውና የዳይመንድ ሊግ መሪ የሆነችው አበባ አረጋዊ እና የቅርብ ተቀናቃኟ ገንዘቤ ዲባባ ከሜዳልያው ባለድርሻ ለመሆን ጠንካራ ፉክክር እንደሚያሳዩ ይጠበቃል፡፡ትናንት የ1500 ሜትር ወንዶች የመጀመርያ ዙር ማጣርያየተካሄደ ሲሆን መኮንን ገብረመድህን፤ ዳዊት ወልዴ እና ተሾመ ዲራርሳ ሲወዳደሩ  ማጣርያውን ካለፉ በግማሽ ፍፃሜ የፊታችን ማክሰኞ ይሰለፋሉ፡፡ የሜዳልያ ፍልሚያው ደግሞ ሀሙስ ይሆናል፡፡ በ1500 ወንዶች ውድድር ላይ በቤጂንግ ኦሎምፒክ አሸናፊ የነበረው ሞሮካዊ አትሌት በዶፒንግ ጥፋት የተነጠቀው የወርቅ ሜዳልያ የወሰደው የኬንያው አዝቤል ኪፕሮፕ በለንደን ኦሎምፒክ በአሳማኝ ሁኔታ በርቀቱ ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ወስዷል፡፡ በሴቶች የ1500 ሜትር የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ሰኞ ይደረግና ግማሽፍፃሜው አርብ እንዲሁም እሁድ የፍፃሜው ውድድር ይካሄዳል፡፡ ዛሬ ጠዋት በ3ሺ ሜትር መሰናክል የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የሴቶች ውድድር ሶፍያ አሰፋ ፤ህይወት አያሌውና  እቴነሽ ዲሮ ተሳተፈዋል፡፡ ይህን የማጣርያ ምእራፍ  ካለፉ በፍፃሜው የሜዳልያ ውድድር የሚሰለፉት ሰኞ ላይ ነው፡፡ በወንዶች የ3ሺ መሰናክል የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ትናንት ተደርጎ ፍፃሜው ደግሞ በነገው እለት ይሆናል፡፡ በ3ሺ መሰናክል በሁለቱም ፆታዎች ለሜዳልያ እድልያላቸው የኬንያ እና የራሽያ አትሌቶች ቢሆኑም ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ግምት ተሰጥቷል፡፡ንዲራ ተሸካሚዋ ያኔትበ30ኛው ኦሎምፒያድ የመክፈቻ ትርኢት የተሳታፊ አገራት ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራየተሸከመችው ዋናተኛዋ ያኔት ስዩም ገብረመድህን ነበረች፡፡ ትውልዷ በኮምበልቻ የሆነችው ያኔት ስዩም ኢትዮጵያን በዋና ውድድር በኦሎምፒክ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ  በመወከል ለሰራችው ፈርቀዳጅ ታሪክ ባንዲራ መሸከሟን ተገቢ ያደርገዋል፡፡ የ18 አመቷ ያኔት ስዩም በኦሎምፒኩ በ50 ሜትር ነፃ ዋና ልትሳተፍ የበቃችው በቂ የስፖርት መሰረተ ልማት እና ስልጠና በሌለበት አገር ነው፡፡ ለ5 ዓመታት ከፍተኛ ጥረት አድርጋ ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ  ስፖርተኞችን ለኦሎምፒክ ተሳትፎ በሚያበቃበት የዩኒቨርሳሊቲ ምለመላ ህግ መሰረት ከሌላው ዋናተኛ ሙሉአለም ድሪባ ጋር በኦሎምፒክ ለመወዳደር በቅተዋል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት በዓለም ሻምፒዮና የአዋቂ እና ወጣት ውድድሮች እንዲሁም በኦል አፍሪካን ጌምስ ኢትዮጵያን በመወከል በውሃ ዋና ውድድሮች ስትሳተፍ የቆየችው ያኔት ስዩም በአገር አቀፍ ደረጃ በስፖርቱ አይነት ያስመዘገበችው ስኬት የኢትዮጵያ ከፍተኛው የዋናተኛ ተውጤት ክብረወሰን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ያኔት ስዩም በአገር ውስጥ ውድድሮችየተሳትፎ ታሪኳ 40 የወርቅ፤ 5 የብርና 4 የነሐስ ሜዳልያዎችን ሰብስባለች፡፡ኃይሌ አፍሪካ ለኦሎምፒክ መሰናዶ  ዝግጁ ናት ይላልበለንደን ኦሎምፒክ በማራቶን ለመሳተፍ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጎ ሳይሳካለት የቀረው ኃይሌ ገብረስላሴ  አፍሪካ ኦሎምፒክን የማዘጋጀት አቅም እንዳለትና ወደ ፖለቲካው በመግባት አገሩን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ፍላጎት እንዳለው ተዘገበ፡፡ ኃይሌ በለንደን ኦሎምፒክ አገሩን ወክሎ ሊሮጥ ባለመቻሉ እንደቆጨው የገለፁ ዘገባዎች ከ4 ዓመት በኋላ ብራዚል በምታስተናግደው 31ኛው ኦሎምፒያድ በ43 አመቱ ማራቶንን ለመሮጥ ፍላጎት  እንዳለው መናገሩን አውስተዋል፡፡ ኃይሌ ምንም እንኳን በለንደን ኦሎምፒክ ለመወዳደር ባይበቃም በታላቁ የስፖርት መድረክ ለከፍተኛ ክብር የሚያበቁ ተሳትፎዎች ነበሩት፡፡ በኦሎምፒኩ የችቦ ጉዞ የተሳተፈው ኃይሌ  በመክፈቻው ስነስርዓት ከተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ባንኪ ሙን፤ ከታዋቂው ቦክሰኛ መሃመድ አሊ እና ከሌሎች እንግሊዛውያን እውቅ ኦሎምፒያኖች ጋር የኦሎምፒክ አርማ ያረፈበትን ነጭ ባንዲራ ይዞ በመሰለፍ በመብቃት ከፍተኛ ሞገስ አግኝቷል፡፡የኦሎምፒክ መድረክ ለወከሉን ኦሎምፒያኖች ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻቸውም የኩራትና የአድናቆት ምንጭ እንደሆነ ለስፖርት አድማስ አስተያየታቸውንና መልካም ምኞታቸውን የገለፁት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ የሚመዘገብ አመርቂ ውጤት ደስታው የአትሌቶቻችን ብቻ አይደለም ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ  እስከዛሬ ከተገኘው የበለጠ የሜዳሊያ ብዛት፣ በወርቅ፣ ብር እና ነሐስ አዲስ ከተሳተፉት አትሌቶቻችን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡ ብዙዎቹ አስተያየት ሰጪዎች  3 እና 4 የወርቅ ፣ 2 የብር እና የ3 ነሐስ ሜዳልያዎችን ተመኝተዋል፡፡  የከተማው ነዋሪዎች ታላቁ የስፖርት መድረክ እድሜ ፤ ፆታ እና ዘር ሳይለዩ በአንድ ላይ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው ሲገልፁ በኦሎምፒክ ሰሞን በአትሌቶች የሚገኝ ስኬት ኢትዮጵያ በድህነቷ ብቻ የምትጠራበትን አሰልቺ ሁኔታ ይቀይራል ሲሉ ኦሎምፒክ አገራችንን ከሌሎች አለም አገራት ጋር የሚያገናኝና የሚያስተዋውቅ በመሆኑ እንደሰትበታለን ብለዋል፡፡ የስፖርት አድማስ ተባባሪ ሪፖርተር የሆነችው ግሩም ተሰማ  በካዛንቺስ፤ በአራት ኪሎ፤ በፒያሳ፤ በአዲሱ ገበያ እና በሌሎች የአዲስ አበባ ስፍራዎች ያነጋገረቻቸው አስተያየት ሰጭዎች  በእነ አበበ ቢቂላ ፈርቀዳጅነት የተጀመረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ገድልና ጀግንነት ኩራታቸው ነው፡፡ የአትሌቶቻችን ጀግንነት  በኦሎምፒክ ሰሞን ብቻ ሳይሆን በማናቸውም አጋጣሚዎቻቸው የሚያስታውሷቸው የማይረሷቸው ትዝታዎቻቸው መሆናቸውን ሲጠቅሱም በተለይ ከአሁኑ ዘመን ኦሎምፒያኖች ለኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ቀነኒሣ በቀለ እና ጥሩነሽ ዲባባ የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

በ4 ኦሎምፒኮች ያልተደፈረው የ10ሺ የወርቅ ክብር ትናንት ምሽት ዓለም በከፍተኛ ጉጉት የጠበቀው የሴቶች 10ሺ ሜትር ተካሂዷል፡፡ የተወዳደሩት ኢትዮጵያውያን ኦሎምፒያኖች ጥሩነሽ ዲባባ ፤ ወርቅነሽ ኪዳኔና በላይነሽ ኦልጅራ ሲሆኖ ውጤታማነታቸው በቀጣይ ውድድሮች ኢትዮጵያ ለሚኖራት ስኬት መነቃቃት እንደሚፈጥር ታምኖበታል፡፡ ውድድሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ሊስብ የቻለው በኢትዮጵያዋ ጥሩነሽ ዲባባ እና በኬንያዋ ቪቪያን ቼሮይት መካከል ከባድ ትንቅንቅ እንደሚታይበት በመጠበቁ ነበር፡፡ በአቴንስ  እና ቤጂንግ ኦሎምፒኮች በ10ሺ ሜትር ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ያላት ጥሩነሽ ዲባባ በትናንቱ ውድድር ሻምፒዮናነቷን ስታስጠበቅ በ3  ኦሎምፒኮች 3 የወርቅ ሜዳልያ  ያገኘች ብቸኛ አትሌት ትሆናለች፡፡ ባለፈው ዓመት ጥሩነሽ በጉዳት ከውድድር በመራቋ  የኬንያዋ አትሌት ቪቪያን ቼሮይት ገንናለች፡፡ በኮርያ ዳጉ በተደረገው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10ሺ እና 5ሺ ሜትር ውድድሮች ድርብ የወርቅ ሜዳልያ ድሎችን በማስመዝገቧም በሁለቱም ርቀቶች በለንደን ኦሎምፒክ ከፍተኛ ግምት እንድታገኝ ምክንያት ሆኗል፡፡ በትራክ ላይ የ10ሺ እና 5ሺ ሜትር 11 ውድድሮች ሁለቱ አትሌቶች ሲገናኙ ሁሉንም ያሸነፈችው ጥሩነሽ ዲባባ ነበረች፡፡ የቀነኒሳ የወርቅ ሜዳልያ ሃትሪክ፤ የወንድማማቾቹ ፍጥጫ እና የሞ ፋራህ ፉከራዛሬ ምሽት ላይ በ10ሺ ሜትር ወንዶች ሌላው ወሳፅ ፍልሚያ ይደረጋል፡፡ ከ1996 የአትላንታ ኦሎምፒክ ጀምሮ 4 የወርቅ ሜዳልያዎችን ሁለቱን በኃይሌ አትላንታ እና ሲድኒ ላይ እንዲሁም ሁለቱን በቀነኒሳ አቴንስ እና ቤጂንግ ላይ ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ በለንደን ይሄው ስኬት ተደግሞ በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ በታሪክ 6ኛውን በተከታታይ 5 ኦሎምፒኮች 5ኛውን የወርቅ ሜዳልያ መገኘቱ ይጠበቃል፡፡ በ10ሺ ሜትር ውድድሩ ኢትዮጵያን ከወከሉት ኦሎምፒያኖች ከፍተኛው ግምት የተሰጠው በርቀቱ 2 የኦሎምፒክና 5 የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያዎችን የሰበሰበው እና የርቀቱን የዓለም እና የኦሎምፒክ ሪከርድ የያዘው የ30 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ ነው፡፡ ከቀነኒሳ ጋር በአስቸጋሪው የ10ሺ ሜትር ውድድር ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ የሚያደርገው ፉክክር ይጠበቃል፡፡ በሜዳልያ ተፎካካሪነት ከኢትዮጵያውያኑ ኦሎምፒያኖች ጋር ስሙ ሊጠቀስ የበቃው ደግሞ እንግሊዝን የሚወክለው ሞፋራህ ብቻ ነው፡፡ በ1968 እኤአ ላይ ሜክሲኮ ኦሎምፒክ ላይ በርቀቱ ብቸኛ የወርቅ ሜዳልያ ያገኘችው  ኬንያ ብዙም አልተገመተችም፡፡ በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በ10ሺ ሜትር ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች በ5ሺ ደግሞ 1 የወርቅ እና 1 የብር ሜዳልያ በማግኘት ከፍተኛውን ውጤት የያዘው ቀነኒሳ በቀለ በዛሬው የ10ሺ ሜትር ውድድሩ በድጋሚ ካሸነፈ የነበረውን የውጤት ክብረወሰኑን ያሻሽላል፡፡ ኃይሌ ገብረስላሴ ሰሞኑን በሰጠው አስተያየት በ10ሺ ሜትር ውድድሩ የወርቅ ሜዳልያው ድል ለቀነኒሳ እንደሚያጋድል መስክሯል፡፡ በውድደሩ የሚኖረው የአሯሯጥ ሁኔታ የፈጠነ ከሆነ ለቀነኒሳ ማሸነፍ ምክንያት እንደሚሆን የገለፀው ኃይሌ ሩጫው ዝግ የሚል ከሆነ  ለእንግሊዛዊው ሞ ፋራህ የማሸነፍ እድል ሊፈጠር እንደሚችል ገምቷል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺ ሜትር ውድድሩ ለማሸነፍ ስላለው ፍላጎት ለጋርድያን ሲገልፅ‹ ታሪክ በልቤ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ በ3 ኦሎምፒኮች 3 የወርቅ ሜዳልያ ለማሳካት መቻል ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሳስብበት ቆይቻለሁ፡፡ የሚሳካልኝ ከሆነ በእውነት ትልቅ ክብር ነው ›ብሏል፡፡እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ባለፈው አመት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ውድድሮች ድርብ የወርቅ ሜዳልያዎችን ወስዷል፡፡  በርቀቱ የእንግሊዝና የአውሮፓ ሪከርዶችን ዘንድሮ ያስመዘገበው  ሞ ፋራህ ስለውድድሩ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ወቅታዊ ብቃቱ  በፈጠረለት የመተማመን ስሜት ለሜዳልያ ድል እንደሚያበቃው ተናግሯል፡፡ ሞ ፋራህ ስለ ቀነኒሳ ተምሳሌትነትም የገለፀው ነገር አለ፡፡ ቀነኒሳ  በአዋቂ ውድድሮች በፍፁም የበላይነት እያሸነፈ በነበረበት ወቅት እኔ በወጣት ውድድሮች ነበርኩ ያለው ሞ ፋራህ ዛሬ በኦሎምፒክ ስንገናኝ ለስፖርቱ ያደረገውን ታላቅ የስኬታማነት አስተዋፅኦ በአርዓያነት እየተመለከትኩ ነው ብሏል፡፡ማራቶን ልእልቷ ትመለስ ይሆን ወደ ቤቷኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ በሴቶች ማራቶን ከፍተኛውን ውጤት ከ16 ዓመታት በፊት በአትላንታ ኦሎምፒክ በፋጡማ ሮባ የወርቅ ሜዳልያ ድል ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ  ነገ በሚካሄደው የሴቶች ማራቶን ይህን ታላቅ ክብር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው ሶስቱ ወጣት ኦሎምፒያኖች የ25 አመቷ ቲኪ ገላና፤ የ26 ዓመቷ አሰለፈች መርጊያ እና የ22 አመቷ ማሬ ዲባባ ናቸው፡፡ ዘንድሮ የሮተርዳም ማራቶንን ያሸነፈችው ቲኪ ገላና በዓለም የማራቶን  ፈጣን ሰዓት 2ኛ ያለውን 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ 58 ሰኮንዶች ያስመዘገበች  በዱባይ ማራቶን 1 እኛ እና ሁለተኛ የወጡት እና በዓመቱ የፈጣን ሰዓት ደረጃ በ4ኛ እና በ6ኛ ደረጃ ላይ የተመዘገቡ ሰዓቶች ያሏቸው አሰለፈች መርጊያ እና ማሬ ዲባባ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ናቸው፡፡ አምና በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን የነሐስ ሜዳልያ ያገኘችው እና በፓሪስ እና የዱባይ ማራቶን ውድድሮች ከፍተኛ ልምድ ያላት አሰለፈች መርጊያ  ሰዓቷ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ1 ሰኮንዶች ነው፡፡ ማሬ ዲባባ በበኩሏ በርቀቱ ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓቷ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ52 ሰኮንዶች ነው፡፡ከ4 ዓመት በፊት በቤጂንግ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን በፀጋዬ ከበደ የተገኘው የነሐስ ሜዳልያ ዘንድሮ በተሻለ ውጤት መደገሙ የሚያጠያይቅ ይመስላል፡፡ዋናው ምክያት ደግሞ በውድድሩ ለሚቀርቡ ሜዳልያዎች ዋንኛዎቹ ተፎካካሪዎች የኬንያ ምርጥ አትሌቶች መሆናቸው በስፋት መገለፁ ነው፡፡ በኦሎምፒኩ የመጨረሻ ቀን ዋዜማ ላይ በሚደረገው የወንዶች ማራቶን  አየለ አብሽሮ፤ ዲኖ ሰፈር እና ጌቱ ፈለቀ ተሳታፊ ናቸው፡፡ ዘንድሮ የዱባይ ማራቶንን ሲያሸንፍ በማራቶን የምንገዜም 4ኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው አየለ አብሽሮ በሜዳልያው ትንቅንቅ ሊገባ እንደሚችል ግምት አለ፡፡ ቤጂንግ ኦሎምፒክ ለኬንያ በታሪክ የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘውን ሳሙኤል ዋንጂሩ ታሪክ ለንደን ላይ ለመድገም ከፍተኛ ግምት ያገኘው ያለፉትን ሁለት የለንደን ማራቶን ውድድሮች ያሸነፈው የ30 ዓመቱ ኬንያዊ ዊልሰን ኪፕሶንግ ነው፡፡ የሁለት ግዚያት የማራቶን የዓለም ሻምፒዮኑ አቤል ኪሪዊምም ይጠበቃል፡፡አስጨናቂው 5ሺ ከ4 ዓመት በፊት በ29ኛው ኦሎምፒያድ ቤጂንግ ላይ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ውድድሮች ድርብ የወርቅ ሜዳልያዎችን ለማስመዝገብ የቻሉት ሁለቱ የኢትዮጵያ ምርጥ ኦሎምፒያኖች ቀነኒሳ በቀለና ጥሩነሽ ዲባባ  በለንደን ኦሎምፒክ ይህን ታሪካዊ ድላቸውን ለመድገም ይጠበቁ ነበር፡፡ ሁለቱ አትሌቶች ተሸንፈው በማያውቁበት የ10ሺ ሜትር ውድድር ትናንት እና ዛሬ በቋሚ ተሰላፊነት ኦሎምፒኩን ቢካፈሉም በ5ሺ ሜትር ተጠባባቂ መሆናቸው ስፖርት አፍቃሪውን ሲያስጨንቅ የሰነበተ ነው በኦሎምፒክ ልኡካን ደንብ መሰረት በየተኛውም ርቀት በተጠባባቂነት የተያዙ አትሌቶች ወደ ኦሎምፒኩ መካሄጃ ከተማ የሚሄዱ ባይሆንም በ10ሺ ሜትር ቋሚ ተሳላፊ የሆኑት ቀነኒሳ ጥሩነሽ በለንደን ይገኛሉ፡፡ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪኳ አቴንስ ላይ በ2004 እኤአ ላይ የነሐስ እንዲሁም ከ4 ዓመት በፊት በቤጂንግ የወርቅ ሜዳልያ የወሰደችና የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን ከያዘች 5 አመታት ያለፋት አትሌት ናት፡፡ በሴቶች 5ሺ ሜትር ኢትዮጵያን በመወከል የሚሮጡት ሶስቱ ኦሎምፒያኖች በ2004 እኤአ አቴንስ ላይ የመጀመርያውን የኢትዮጵያ 5ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ በሴቶች ያስገኘችው መሰረት ደፋር፤ በ1500 ሜትር የዓለም ኢንዶር ሻምፒዮን የሆነችው ገለቴ ቡርቃ እና ወጣቷ እና በኦሎምፒክ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ የምትሰለፈው ገነት ያለው ናቸው፡፡ የቋሚ ተሰላፊዎቹ ምርጫ  ሰዓትን የተንተራሰ ሲሆን ሶስቱ አትሌቶች በሮም ዳይመንድ ሊግ ውድድር ከ1 እሰከ 3 ሲወጡት የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች በማስመዝገባቸው ነው፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ ዘንድሮ በ5ሺ ሜትር አንድ ውድድር በኒውዮርክ ዳይመንድ ሊግ አድርጋ ስታሸንፍ ያስመዘገበችው ሰዓት በአመቱ ለኢትዮጵያውን አትሌቶች 4ኛው ፈጣን ሰዓት ስለነበር በተጠባባቂነት ተይዛለች፡፡በወንዶች 5ሺ ሜትር የተያዙት በኦሎምፒክ መድረክ የመጀመርያ ተሳትፎ የሚያደርጉት እና በውድድር ዘመኑ በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ምርጥ ብቃት ይዘው የሚገኙት ሶስት አትሌቶች ናቸው፡፡ ሶስቱ አትሌቶች  የዘንድሮውን ዳይመንድ ሊግ የሚመራው ደጀን ገብረመስቀል፤ በሀለተኛ ደረጃ የሚገኘው ሐጎስ ገብረ ህይወት እና የኔው አላምረው ናቸው፡፡ አትሌቶቹ በ5ሺ ሜትር ቋሚ ተሰላፊ ሆነው ሊመረጡ የበቁት በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ከ1 እሰከ 3 ተከታትለው ሲገቡ ከ12.50 ደቂቃዎች በታች  በመግባት የመጀመርያዎቹን ሶስት የኢትዮጵያ የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች በማስመዝገባቸው ነው፡፡ በ5ሺ ሜትር የዓለም እና የኦሎምፒክ ሪከርዶችንና የሻምፒዮናነት ክብሮች የያዘው አትሌት ቀነኒሳ በበኩሉ በርቀቱ በኢትዮጵያ የዓመቱ 5ኛው ፈጣን ሰዓትን ማስመዝገቡ ተጠባባቂ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ የሴቶች 5ሺ  የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ማክሰኞ ይደረግና የሜዳልያው ፍልሚያ የነገ ሳምንት ይሆናል፡ በ5ሺ ሜትር ወንዶች የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ረቡእ ተደርጎ የሜዳልያ ትንቅንቁ በመቀጠል በሚመጣው ሰኞ ይሆናል፡፡ በመካከለኛ ርቀቶች በ800፤ በ1500ሜ እና በ3ሺ መሰናክል

በ30ኛው ኦሎምፒያድ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ልዩ ያደረጉት በሜዳልያ ተስፋ የገቡ ኦሎምንፒያኖች የሚካፈሉባቸው የመካከለኛ ርቀት የአትሌቲክስ ውድድሮች ናቸው፡፡ በተለያዩ ሁኔታዎች በመካከለኛ ርቀት በተሰሩ የሜዳልያ ትንበያዎችና ግምቶች የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ እድል ያልተጠበቀ ሲሆን የብርና የነሐስ ሜዳልያ ድሎች ግን በ1500 ሴቶች፤ በ3ሺ መሰናክል ሴቶች እና በ800 ሜትር ወንዶች ግምት ተሰጥቷል፡፡

በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ሚኒማውን አሟልተው ለመሰለፍ የሚበቁት የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በሴቶች ፋንቱ ሚጌሶ እና በወንዶች መሃመድ አማን ናቸው፡፡ በወንዶች 800 ሜትር የኢትዮጵያን ሪከርድ የያዘው መሃመድ አማን  ለወርቅ ሜዳልያ ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን የኬንያ አትሌት ዴቪድ ሩዲሻ ለመቀናቀን ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ከአመት በፊት ከ35 ውድድሮች ያለመሸነፍ ቆይታ በኋላ ዴቪድ ሩዲሻ የተሸነፈው በመሃመድ አማን ነበር፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ ለዴቪድ ሩዲሻ እና ለመሃመድ አማን ፉክክር ትኩረቱ ቢያመዝንም የሱዳኑ አቡበከር ካኪም በተፎካካሪነት ይጠቀሳል፡፡ በሴቶች 800 ሜትር አዲስ ታሪክ ለኢትዮጵያ እንደምትሰራ ከፍተኛ እምነት ያሳደረችው ፋንቱ ሚጌሶ በሜዳልያ ፉክክሩ ለመግባት ከባድ ፈተና የሚጠብቃት ይመስላል፡፡ በርቀቱ የኦሎምፒክ ሻምፒዮናዋ ኬንያዊት ፓሜላ ጄሊሞ፤ የዓለም ሻምፒዮናዋ ራሽያዊት ማርያ ሳቪኖቫ፤ የአሜሪካዋ አሊሽያ ሙንቶኖ እና የደቡብ አፍሪካዋ ካስተር ሴማንያ የሜዳልያ እድላቸው በስፋት ግምት ያገኘ ነው፡፡በ800 ሜትር የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ሰኞ ከተካሄደ በኋላ ግማሽ ፍፃሜው በማግስቱ ተደርጎ የሜዳልያ ትንቅንቁ ሀሙስ ይወሰናል፡፡ በተመሳሳይ ርቀት በሴቶች ምድብ የመጀመርያ ዙር በመጭው አርብ ተደርጎ ግማሽ ፍፃሜው የዛሬ ሳምንት ይደረግና ፍፃሜው ከ2 ቀናት በኋላ ነው፡፡በ1500ሜ ትር ከፍተኛ የሜዳልያ ተስፋ ሊኖራት የሚችለው በሴቶች ምድብ ቢሆንም ያመቱን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሞሮካዊ አትሌት ማድያም ሲሊቫሊ ለወርቅ ሜዳልያው ዋና ተቀናቃኝ ተደርጋለች፡፡ በውድድር ዘመኑ ከየትኛው አትሌት በላቀ ብዙ ውድድሮች ያሸነፈችውና የዳይመንድ ሊግ መሪ የሆነችው አበባ አረጋዊ እና የቅርብ ተቀናቃኟ ገንዘቤ ዲባባ ከሜዳልያው ባለድርሻ ለመሆን ጠንካራ ፉክክር እንደሚያሳዩ ይጠበቃል፡፡ትናንት የ1500 ሜትር ወንዶች የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የተካሄደ ሲሆን መኮንን ገብረመድህን፤ ዳዊት ወልዴ እና ተሾመ ዲራርሳ ሲወዳደሩ  ማጣርያውን ካለፉ በግማሽ ፍፃሜ የፊታችን ማክሰኞ ይሰለፋሉ፡፡ የሜዳልያ ፍልሚያው ደግሞ ሀሙስ ይሆናል፡፡ በ1500 ወንዶች ውድድር ላይ በቤጂንግ ኦሎምፒክ አሸናፊ የነበረው ሞሮካዊ አትሌት በዶፒንግ ጥፋት የተነጠቀው የወርቅ ሜዳልያ የወሰደው የኬንያው አዝቤል ኪፕሮፕ በለንደን ኦሎምፒክ በአሳማኝ ሁኔታ በርቀቱ ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ወስዷል፡፡ በሴቶች የ1500 ሜትር የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ሰኞ ይደረግና ግማሽፍፃሜው አርብ እንዲሁም እሁድ የፍፃሜው ውድድር ይካሄዳል፡፡ ዛሬ ጠዋት በ3ሺ ሜትር መሰናክል የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የሴቶች ውድድር ሶፍያ አሰፋ ፤ህይወት አያሌውና  እቴነሽ ዲሮ ተሳተፈዋል፡፡ ይህን የማጣርያ ምእራፍ  ካለፉ በፍፃሜው የሜዳልያ ውድድር የሚሰለፉት ሰኞ ላይ ነው፡፡ በወንዶች የ3ሺ መሰናክል የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ትናንት ተደርጎ ፍፃሜው ደግሞ በነገው እለት ይሆናል፡፡ በ3ሺ መሰናክል በሁለቱም ፆታዎች ለሜዳልያ እድል ያላቸው የኬንያ እና የራሽያ አትሌቶች ቢሆኑም ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ግምት ተሰጥቷል፡፡ባንዲራ ተሸካሚዋ ያኔትበ30ኛው ኦሎምፒያድ የመክፈቻ ትርኢት የተሳታፊ አገራት ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ የተሸከመችው ዋናተኛዋ ያኔት ስዩም ገብረመድህን ነበረች፡፡ ትውልዷ በኮምበልቻ የሆነችው ያኔት ስዩም ኢትዮጵያን በዋና ውድድር በኦሎምፒክ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ  በመወከል ለሰራችው ፈርቀዳጅ ታሪክ ባንዲራ መሸከሟን ተገቢ ያደርገዋል፡፡ የ18 አመቷ ያኔት ስዩም በኦሎምፒኩ በ50 ሜትር ነፃ ዋና ልትሳተፍ የበቃችው በቂ የስፖርት መሰረተ ልማት እና ስልጠና በሌለበት አገር ነው፡፡ ለ5 ዓመታት ከፍተኛ ጥረት አድርጋ ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ  ስፖርተኞችን ለኦሎምፒክ ተሳትፎ በሚያበቃበት የዩኒቨርሳሊቲ ምለመላ ህግ መሰረት ከሌላው ዋናተኛ ሙሉአለም ድሪባ ጋር በኦሎምፒክ ለመወዳደር በቅተዋል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት በዓለም ሻምፒዮና የአዋቂ እና ወጣት ውድድሮች እንዲሁም በኦል አፍሪካን ጌምስ ኢትዮጵያን በመወከል በውሃ ዋና ውድድሮች ስትሳተፍ የቆየችው ያኔት ስዩም በአገር አቀፍ ደረጃ በስፖርቱ አይነት ያስመዘገበችው ስኬት የኢትዮጵያ ከፍተኛው የዋናተኛ ተውጤት ክብረወሰን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ያኔት ስዩም በአገር ውስጥ ውድድሮች የተሳትፎ ታሪኳ 40 የወርቅ፤ 5 የብርና 4 የነሐስ ሜዳልያዎችንሰብስባለች፡፡

ኃይሌ አፍሪካ ለኦሎምፒክ መሰናዶ  ዝግጁ ናት ይላልበለንደን ኦሎምፒክ በማራቶን ለመሳተፍ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጎ ሳይሳካለት የቀረው ኃይሌ ገብረስላሴ  አፍሪካ ኦሎምፒክን የማዘጋጀት አቅም እንዳለትና ወደ ፖለቲካው በመግባት አገሩንበፕሬዝዳንትነት ለመምራት ፍላጎት እንዳለው ተዘገበ፡፡ ኃይሌ በለንደን ኦሎምፒክ አገሩን ወክሎ ሊሮጥ ባለመቻሉ እንደቆጨው የገለፁ ዘገባዎች ከ4 ዓመት በኋላ ብራዚል በምታስተናግደው 31ኛው ኦሎምፒያድ በ43 አመቱ ማራቶንን ለመሮጥ ፍላጎት  እንዳለው መናገሩን አውስተዋል፡፡ ኃይሌ ምንም እንኳን በለንደን ኦሎምፒክ ለመወዳደር ባይበቃም በታላቁ የስፖርት መድረክ ለከፍተኛ ክብር የሚያበቁ ተሳትፎዎች ነበሩት፡፡ በኦሎምፒኩ የችቦ ጉዞ

የተሳተፈው ኃይሌ  በመክፈቻው ስነስርዓት ከተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ባንኪ ሙን፤ ከታዋቂው ቦክሰኛ መሃመድ አሊ እና ከሌሎች እንግሊዛውያን እውቅ ኦሎምፒያኖች ጋር የኦሎምፒክ

አርማ ያረፈበትን ነጭ ባንዲራ ይዞ በመሰለፍ በመብቃት ከፍተኛ ሞገስ አግኝቷል፡፡

 

 

Read 16582 times Last modified on Saturday, 04 August 2012 13:09