በዳጉ ኮሙኒኬሽን በየወሩ የሚካሄደው የሚዲያ ባለሙያዎች ወርሃዊ መድረክ “ሚዲያ የማን ነው?” በሚል ርዕስ ትላንት ቦሌ በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል አካሄደ። በመርሃ ግብሩ ላይ በርካታ እንግዶችና ጋዜጠኞች የታደሙ ሲሆን የሚዲያ ሚና ምንድን ነው? ሚዲያ የማን ነው? በሚሉና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ የልምድ ልውውጥ መደረጉን የዳጉ ኮሙኒኬሽን መስራችና ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ ገልጿል።
ዳጉ በቀጣይ ወርም በተመረጠ ርዕስ ውይይቱን በማካሄድ የሚዲያ ባለሙያዎችን መድረክ እየፈጠረ በማወያየት ሚዲያው አካባቢ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ለማጥበብ እንደሚጥር ጋዜጠኛ ማናዬ ጨምሮ ገልጿል።
Saturday, 28 November 2020 00:00
“ዳጉ” ወርሃዊ የጋዜጠኞች መድረክ ትላንት ተካሄደ
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና