Thursday, 05 November 2020 00:00

4500 ፓውንድ በውስጥ ሱሪያቸው ደብቀው የተገኙ የብራዚል ፖለቲከኛ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዋነኛ አጋር እንደሆኑ የሚነገርላቸው አንድ የአገሪቱ ፖለቲከኛ፤ በጸረ-ሙስና ባለሥልጣናት በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ በርካታ የገንዘብ ኖቶች ከተገኘባቸው በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተዘግቧል፡፡  
በመጀመሪያ ላይ 1ሺ 380 ፓውንድ እና 4ሺ 650 ፓውንድ ነው በሴናተር ቺኮ ሮድሪጉ መኖሪያ ቤት ካዝና ውስጥ የተገኘው ተብሏል፤ባለፈው ረቡዕ ፖሊስ በመኖሪያ ቤታቸው ባደረገው ፍተሻ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አላበቃም፡፡
ሴናተሩ ወደ መታጠቢያ ክፍል እንዲሄዱ የተጠየቁ ሲሆን በእርምጃቸው ወቅትም በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ ትልቅ ባለ አራት ማዕዘን ቅርጽ፣ የታሰረ ነገር መደበቃቸውን፣ አንድ የፖሊስ ኃላፊ ይደርስበታል፡፡   
“ከውስጥ ሱሪያቸው ከመቀመጫቸው አካባቢም ባጠቃላይ 2ሺ ፓውንድ ተገኝቷል” ይላል፤ የፖሊስ ሪፖርት፡፡
ከዚያም ተጨማሪ ገንዘብ በውስጥ ሱሪያቸው ውስጥ ይኖር እንደሆነ ለሦስተኛ ጊዜ ተጠየቁ፡፡ በጥያቄው የተበሳጩት ሴናተሩ፤ እየተነጫነጩ እጃቸውን ወደ ውስጥ ሱሪያቸው ይልካሉ፡፡ እጃቸው ባዶውን አልተመለሰም፡፡ ሌላ 2ሺ 500 ፓውንድ ጎትቶ አወጣ፡፡ ከዚያ በኋላ በተደረገ ፍተሻም፣ 35 ፓውንድ መገኘቱን ፖሊስ ጠቁሟል። በአሁኑ ሰዓት ሴናተር ቺኮ ሮድሪጉ፣ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ ታውቋል፡፡


Read 5018 times