Tuesday, 03 November 2020 00:00

ዘጠኝ የአሜሪካ ቢሊየነሮች በ1 ቀን ብቻ 14 ቢሊዮን ዶላር ከስረዋል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የፌስቡኩን መስራች ማርክ ዙከርበርግና የማይክሮሶፍቱን መስራች ቢል ጌትስን ጨምሮ 9 አሜሪካውያን ቢሊየነሮች ባለፈው ሰኞ ብቻ በድምሩ 14 ቢሊዮን ዶላር ያህል ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡
በዕለቱ በአሜሪካ የተለያዩ የአክሲዮን ገበያዎች የዋጋ ቅናሽ መከሰቱን ተከትሎ፣ ቢሊየነሮቹ በድምሩ 14 ቢሊዮን ዶላር መክሰራቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ማርክ ዙከርበርግ ከፍተኛውን የ2.8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመው አመልክቷል፡፡
ቢል ጌትስ ሰኞ ዕለት ሃብቱ በ1.7 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 115 ቢሊዮን ዶላር ያህል መድረሱን የገለጸው ዘገባው፤ ከአስሩ የአሜሪካ ዋነኛ ባለጸጎች መካከል በዕለቱ የሃብት መጠኑ የጨመረው የአማዞኑ መስራች ጄፍ ቤዞስ ብቻ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

Read 4303 times