የፊልሙ ዲያሬክተር ዴ ሱዛ፤ በናይሮቢ ጎስቋላ መንደሮች የሚኖረውን ደሃውን ጆርጅ የተባለና በእናቱ የሚዛመደውን የኦባማ ወንድም ቃለምልልስ ያደረገለት ሲሆን አሜሪካ ባራክ ኦባማን በድጋሚ ከመረጠች ምን ክፉ እጣ እንደሚገጥማት በሚያሳዩ ትእይንቶች መታጀቡን ፎክስ ኒውስ አብራርቷል፡፡ በፀረ ኦባማ እንቅስቃሴ የተፈረጀው ዶክመንታሪው፤ ሰሞኑን በሰሜን አሜሪካ 400 ሲኒማ ቤቶች መታየት የጀመረ ሲሆን በገቢው እየተሳካለት ግን አይደለም፡፡ በፖለቲካ ጭብጦች የሚሰሩ ዶክመንታሪዎችን ለሲኒማው ኢንዱስትሪ በማስተዋወቅ ፈርቀዳጅ የተባለው በፀረ ጆርጅ ቡሽ ፊልሙ ከፍተኛ እውቅና ያገኘው ማይክል ሙር ሲሆን በ2004 እ.ኤ.አ ለእይታ የበቃለት ዶክመንታሪ በዓለም ዙርያ እስከ 141 ሚሊዮን ዶላር ማስገኘቱ ይታወሳል፡፡