Friday, 23 October 2020 14:05

በቤጂንግ አሽከርካሪ አልባ ታክሲዎች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አፖሎ ጎ የተባለው የቻይና ኩባንያ ያሰማራቸው አሽከርካሪ አልባ ታክሲዎች ከቀናት በፊት በርዕሰ መዲናዋ ቤጂንግ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተነግሯል፡፡
ታክሲዎቹ ያለ አሽከርካሪ እገዛ በቴክኖሎጂ ብቻ ታግዘው የሚሰጡት አገልግሎት ተሳፋሪዎችን ለአደጋ እንዳያጋልጥ ከ60 ጊዜያት በላይ የደህንነት ፍተሻ እንደተደረገባቸውና ጥራታቸው እንደተረጋገጠ ቻይና ዴይሊ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል፡፡
ተሳፋሪዎች በሞባይል አፕሊኬሽን አማካይነት ታክሲዎችን በመጥራትና መዳረሻቸውን በመሙላት በአፋጣኝ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የጠቆመው ዘገባው፣ ያም ሆኖ ግን አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 60 አመት የሆናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ መሆናቸውን አመልክቷል፡፡
“ሲና ቪሄክል” የተባለው የአገሪቱ ኩባንያ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች አዲሱን አገልግሎት መጠቀም እንደሚፈልጉ ለማወቅ በሰራው የዳሰሳ ጥናት፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አገልግሎቱን ለመጠቀም እንደሚፈልጉ ያም ሆኖ ግን የደህንነት ጉዳይ አንደሚያሳስባቸው መናገራቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

Read 1041 times