Monday, 19 October 2020 00:00

በቤንሻንጉል ጥቃት የተጠረጠሩ 504 ሰዎች ተይዘዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

  የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ 9.4 ቢሊዮን ብር በሚደርስ የሙስና ወንጀል ላይ የምርመራ ስራ እያከናወኑና እንደሚገኝ ትናንት በሰጠው መግለጫ ያስታወቀ ሲሆን በ207 ሚሊን ብር ክፍያ በተጠረጠሩ የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ምርመራ ተጠናቆ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ ጀነራልና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኋላፊ ዘላለም መንግስቴ የ2013 በጀት ዓመቱን የመጀመሪያ  ሩብ ዓመት አፈጸጸም አስመልክቶ ትናንት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት፤ መግለጫ በሩብ ዓመቱ በተደረገው ምርመራ በ207 ሚሊዮን ብር ዝርፊያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረት ተችሏል ብለዋል።
በሌሎች ተቋማት ላይ የተደረጉ ምርመራ ተከትሎ የ9. 4 ቢሊዮን ብር  የሙስና ወንጀል ክስ ለመመስረት የኦዲት ሪፖርት እየጠበቀ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራሉ አስታውቀዋል፡
 ባለፉት ሶስት ወራት በ501 ልዩ ልዩ የወንጀል መዝገቦች ላይ ምርመራ በማድረግ ክስ እንዲመሰረት ለአቃቢ ህግ መተላለፉን ም/ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተጣራባቸው የሚገኙና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ 711 መዝገቦች መኖራቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በፌደራል ደረጃ  ።
በተጨማሪም በወንጀል የተጠረጠሩ 1ሺ 105 ግለሰቦች እየተፈለጉ መሆኑን በቅርቡ በቤኒሻንጉል  ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር   በተያያዘም በግድያ የተጠረጠሩ 504 ሰዎች በቁጥጥር ስር  መዋላቸው ተመልክቷል።
 ከቤኒሻንጉል ጉምዝ  የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ፣ በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ.ር ዐቢይ አህመድ የአማራና የቤንሻንጉል  ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጋር በፅህፈት ቤታቸው ማነጋገራቸውን በፌስቡክ ገፃቸው ጠቁመዋል። በውይይቱም ግጭቶችን በዘላቂነት ማስቆም በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል ጠ/ሚኒስትሩ ።  

Read 10434 times