Saturday, 10 October 2020 12:29

ሴራሊዮን ለሰራተኞች "እጅግ አደገኛ" አገር ተባለች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ሰራተኞች ደህነት የማይጠበቁባቸውና ለስራ እጅግ አደገኛ የሆኑ የአለማችን አገራት ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ ሴራሊዮን በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በሴራሊዮን 69 በመቶ ያህል ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ ሆነው የከፋ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የተገለጸ ሲሆን በጋምቢያ 64 በመቶ፣ በማላዊ ደግሞ 62 በመቶ ያህሉ አደጋው እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡
ሊዮልድ ሬጂስተር ፋውንዴሽን የተባለው የጥናት ተቋም በ142 የአለማችን አገራት ውስጥ ከሚገኙ 150 ሺህ ሰራተኞች ያገኘውን መረጃ መሰረት አድርጎ ባወጣው አለማቀፍ የስራ ላይ ደህንነት ሪፖርት እንዳለው፣ ከአለማችን አጠቃላይ ሰራተኞች 19 በመቶ ያህሉ በስራ ገበታቸው ላይ እያሉ ቢያንስ አንድ ጊዜ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
በድሃና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የአለማችን አገራት ለሰራተኞች እጅግ አደገኛ ከሆኑት የስራ መስኮች መካከል ግብርና እና አሳ አጥማጅነት ይገኙበታል ያለው ሪፖርቱ፣ በጥናቱ ከተካተቱት መካከል 23 በመቶ ወንዶች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው መናገራቸውን አመልክቷል፡፡ በአንዳንድ ጥናቱ የተሰራባቸው አገራት ከአካላዊ ጉዳት ባለፈ 50 በመቶ ያህል ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ ሆነው የተለያዩ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው መረጋገጡም ተነግሯል።

Read 1792 times