Print this page
Tuesday, 06 October 2020 07:56

የወንዶች የስነተዋልዶ ጤና እግር

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ይህን ጽሁፍ በYaleNews በSeptember 15, 2020 ለንባብ ያሉት Mike Cummings ሲገልጹ የጥናቱ ባለቤት የሆኑት sociologist Rene Almeling በመጀመሪያ አንድ ሰው አነጋግረው ነበር። ሰው የው ከሚስቱ ጋር በጋራ ልጅ እንዲኖራቸው የሚፈልግ ሰው ነው፡፡ ፀሐፊዋ ስለኑሮው እንዲብ ራራላቸው በመጋበዝ እያንዳንዱን የህይወቱን እንቅስቃሴ ማለትም ስለገላው አሰተ ጣጠብ፤ ስለ አመጋገቡ፤ ሰአቱን በደስታ ለማሳለፍ ጭማቂ እንደሚጠቀም ሁሉ ከገለጸ በሁዋላ ነገር ግን በደስታ ቢኖርም ጤንነቱን በተመለከተ እንዲሁም ባለው የህይወት ልምድ ልጅ ማግኘት አለ መቻሉን ምናልባት ቢረገዝ እንኩዋን ሲወለድ ችግር እንደሚፈጠር፤ ወይንም ሕመምተኛ የሆነ ህጻን ማጋጠሙ እንደሚያሳዝነው ተረድተዋል፡፡
ጸሐፊዋ  Rene በዚህ ሳይረኩ ሌላ ሰው በሃሳብ ለማገኘት ሞከሩ፡፡ ምክንያታቸውም ያነጋገሩት ሰው የሰጣቸው ምላሽ ትክክለኛውን ነገር ሊወክልላቸው ስላልቻለ ነው፡፡ ወንዶች በአሁኑ ወቅት ስለስነተዋልዶ ጤንነታቸው ውስን የሆነ እውቀት እንዳላቸው ግልጽ ነው፡፡ የሚኖሩበት አካባቢ ወይንም የሚሰሩት ስራ፤ ጤንነታቸው፤ የሚወስዱአቸው መድሀኒቶች የመሳሰሉት ነገሮች የዘር ፈሳሽን (sperm) ሁኔታ እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል እና ልጅ እንኩዋን ቢወለድ በምን ሁኔታ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ትክክለኛውን ነገር ለማወቅ የሚጥሩ ብዙ ወንዶች የሉም Almeling እንደሚገልጹት፡፡
Almeling, an associate professor of sociology, public health, and medicine, GUYnecology: The Missing Science of Men’s Reproductive Health የተሰኘው  መጽ ሀፋቸው የታተመው በ California Press ሲሆን በመጽሐፉም የህክምና ባለሙያዎች  ለወን ዶች የስነተዋልዶ ጤንነት ጉዳይ መጠነኛ ትኩረት ብቻ መስጠታቸው ለምንድነው ሲሉ ይጠይ ቁና ይህ ማለት ደግሞ ለወንዶች፤ለሴቶች ብሎም ለህብረተሰቡ የሚያበረክተውን ጎጂ አስተዋጽኦ ይጠቅሳሉ፡፡ ባለሙያዋ ከ YaleNews ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሀሳባቸውን እንደሚከተለው ገልጸዋል፡፡
የወንዶችን የስነተዋልዶ ጤንነትን በሚመለከት ሳይንሱ ብዙ ትኩረት አለመስጠቱን በሚመለከት ምርምር ለማድረግ ምን ገፋፋዎት?
እኔ ለማየት የሞከርኩት እና መረዳት የፈለግሁት ከሴቶች ጋር ሲነጻጸር ለወንዶች የስነተዋልዶ ጤንነት ሳይንሱ የሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑን እና በውጤቱ ደግሞ ለጤንነት የሚሰ ጠውን አገልግሎት፤የስርአተ ጾታው gender ልማድና የስነተዋልዶው ፖሊሲ ምን ያህል እንደሚጎዳ ነው፡፡ ምርምሩን በማካሂድበት ወቅት የህክምናውን ታሪክ በማስቀደም የማይመጣ ጠነውን የሴቶችን የማህጸንና ጽንስ ሕክምናን ታሪክና የማይመጣጠነውን የወንዶችን የስነተ ዋልዶ ጤና የ50 አመት ታሪክ እንዲሁም የተደረጉ ጥናቶች ካሉ እና መገናኛ ብዙን የዘገቡትን ሁሉ ለመመልከት ችያለሁ፡፡ በዚህ ሂደትም በስተመጨረሻ ወንዶች በዚህ ጉዳይ እውቀታቸው ምን ያህል እንደሆነና በስነተዋልዶ ጤንነታቸው ጉዳይ ላይ ምን እንደሚያስቡ ጠይቄአቸዋለሁ ብለዋል Almeling.
ይህ ጉዳይ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
በቅርብ ጊዜ የሚደረጉ ጥናቶች የወንዶች ጤንነት ገና ከጅምሩ የዘር ፈሳሻቸውን ሊያዛባ እና በውጤቱም የልጅን ጤንነት ሊጎዳ እንደሚችል ያሳያል፡፡ ይህም የወንዶችን እድሜ፤አንዳንድ ባህርያት ለምሳሌም መጠጥ የሚጠጣ ከሆነ፤አንዳንድ እጾችን የሚጠቀም ከሆነ፤ሲጋራ ማጤስ እንዲሁም ለተለያዩ ኬሚካሎች በቤታቸው ወይንም በስራ ቦታ፤ በመኖሪያ አካባቢ የሚጋለጥ ከሆነ ለችግሩ ሊጋለጡ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት፡፡ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ካልሆነ የዘር ፈሳሽ የሚፈጠር እርግዝና ጽንሱ ሊሞት ወይንም ከክብደት በታች የሆነ ልጅ ሊወለድ እና የተወለደው ልጅ ጤነኛ ያለመሆን እድል ሊያጋጥመው እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህ የወንዶች የስነተዋልዶ ጤንነትን ጉዳይ ችላ ማለት በወንዶቹም፤ በልጆቻቸውም ጤንነት ላይ የሚመጣውን የጤንነት ችግር በጸጋ ለመቀበል እንደመዘጋጀት ስለሚሆን ልዩ ትኩረትን ይሻል፡፡ የወንዶች የስነተዋልዶ ጤንነትን አስቀድሞ መመልከት ከተቻለ ግን የወንዶቹንም የሚወለዱ ትም ህጻናት ጤንነት ለማሻሻል ወይንም ለመጠበቅ ያስችላል፡፡ በዚሁ ሳይንቲስቶችና በህክምና ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች በሚያደርጉዋቸው ጥናቶች ስለወንዶች የስነተዋልዶ ጤና እንዲመለ ከቱ በዚሁ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ በሴቶች ብቻ የሚተኮር ከሆነ ግን ግማሹን ማለትም የወንዶችን የስነተዋልዶ ጤና ሳንመለከተው እንዳንቀር እና ጉዳቱ እንዳይቀጥል ልብ ማለት ይገባል ብለዋል ፡፡
የወንዶች የስነተዋልዶ ጤና ትኩረት ማጣት ያስከተለው ችግር ምንድነው?
ሲጀመር ይላሉ ፀሐፊዋ ለምሳሌ እስከዛሬ ድረስ የወንዶች ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ የለም፡፡ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለወንዶች የተገኘው መከላከያ ኮንዶም እና ቫዜክቶሚ የተባለ በቀላል የቀዶ ሕክምና የሚሰራ ዘዴ ነው፡፡ ለሴቶች የስነተዋልዶ ጤና ግን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ጭምር የተለያዩ መከላከያዎች እየተሰሩ ጥቅም ላይ ውለዋል። በውጤቱም ሴቶች እርግዝናን ለመከላከል ወይንም ማርገዝ የማይችሉ ከሆነ የሚታከሙበት ዘዴ እንዲሁም ማርገዝ እንዲችሉና ልጅ እንዲወልዱ የሚያስችል ሳይንሳዊ ግኝቶች ተመዝግበዋል፡፡
ለወንዶች የስነተዋልዶ ጤና ትኩረት ካለመስጠት ጋር በተያያዘ ያለው የእውቀት ክፍተት ምን ይመስላል?
የእውቀት ክፍተቱ በመላው ህብረተሰብ ዘንድ የሚታይ ነው፡፡
የህክምና ባለሙያዎች እንደአስፈላጊ ነገር አድርገው ችግር ከመከሰቱ በፊት ለወንዶች ስለ ስነተዋልዶ ጤናቸው አያወሩአቸውም፡፡
የወንዶን የስነተዋልዶ ጤንነት በሚመለከት ስለ ዘር ፈሳሽ (sperm)ጤንነት የህብረተሰብ ጤና የእውቀት ዘመቻ ( campaign) ሲደረግ አይታይም፡፡
እውቀቱ በህብረተሰቡ ዘንድ እንዳልተንሰራፋ ማሳያው ለጥናቱ ቃለመጠይቅ ካደረግሁላቸው ወንዶች የተገኘው መልስ ነው፡፡ 40 ወንዶችን ስለስነተዋልዶ ጤንነታቸው ሳነጋግራቸው የሰጡኝ መልስ በአብዛኛው ስለዘር ፈሳሻቸው ጤንነትም ሆነ እድገት እውቀት እንደሌላቸው ነው፡፡ አብዛኞቹ መልስ የሰጡኝ ወንዶች እንደመሰከሩት ከሆነ ገና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርታ ቸውን እየተከታተሉ ከሰሙት በስተቀር ሌላ ጊዜ ማንም ነግሮአቸው እንደማያውቅ ነው፡፡
በዘመኑ የተከሰተው ወረርሽኝ COVID-19 የአንድ ሰው ጤንነት የግሉ ወይንም የእያንዳ ንዱ ሰው የራሱ ጉዳይ ነው የማይባልና የግል ምርጫ ተደርጎ ሊወሰድ የማይቻል መሆኑን ለመላው አለም በተመሳሳይ ጊዜ አስተምሮአል ይላሉ ፀሐፊዋ፡፡ ከዚህም አንጻር ማንኛውም ሕመም በተለ ይም የስነተዋልዶ ጤና ችግር የወንዶች ወይንም የሴቶች የራሳቸው ጉዳይ ተብሎ የማይወሰድ እና አንዳቸው ስለአንዳቸው ሊጨነቁበት የሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም ውጤቱ ከግል ጤንነታቸው ባለፈ የሁለቱንም ቤተሰብ የሚመለከት ስለሆነ ነው፡፡
ስለዚህም በወንዶች የስነተዋልዶ ጤንት ጉዳይ ላይ ማተኮር በብዙ መንገዶች ሊገለጽ ይችላል፡፡
የጤና ባለሙያዎች የሴቶች የስነ ተዋልዶ ጤንት ችግርን በሚመለከት ለተገልጋዮች መረጃ በሚሰጡበት ጊዜ ወይንም በሌላ አደረጃጀት ስለወንዶች የዘር ፍሬ ጤንነት ሁኔታ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡
በጤናው ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ባለሙያዎች ወንዶች በእድሜያቸው፤በአኑዋኑዋራቸው፤እና በጤንነታቸው፤ ባጠቃላይም በሚያጋጥማቸው ተጋላጭነት ሳቢያ ሊደርስ የሚችለውን የስተዋልዶ ጤና ችግር መመርመርና ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችና ባለሙያዎች እና ሌሎችም  ሁሉ የወንዶች የስነተዋልዶ ጤንነት ችግር በምን መንገድ የልጆችን ጤንነት እንደሚጎዳ ህብረተሰቡ እንዲያውቅ ማስተማር ስለሚገባቸው የማስተማሪያ ግብአቶችን መቅረጽና ማሰራጨት ይጠበቅ ባቸዋል፡፡
ባጠቃላይም የስነተዋልዶ ጤንነትን ችግር ሙሉ በሙሉ መፍታት ወይንም ከዜሮ ደረጃ ማድረስ አይቻልም፡፡ ነገር ግን የወንዶችን የስነተዋልዶ ጤንነት በሚመለከት ትኩረት ማድረግ የቀጣዩን ትውልድ ጤንነት ለማረጋገጥ ይረዳል ብለዋል Almeling, an associate professor of sociology, public health, and medicine,  


Read 8291 times