Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 July 2012 10:43

ሴት ደራስያን ማህበር በሻሸመኔ ቅርንጫፍ ሊከፍት ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር በሻሸመኔ ከተማ አዲስ ቅርንጫፍ ማህበር ሊከፍት ነው፡፡ የማህበሩ  ቅርንጫፍ ማህበር ነገ በሻሸመኔ ባህል አዳራሽ ከቀኑ 9 ሰዓት ሲከፈት የምስረታ ሥነ ፅሑፋዊ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ማህበሩ በመጪው አርብ “በአይነት እንጀራ” የተሰኘ የመረጃ መፅሐፍ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ ሬዲዮ ፋና ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመፃሕፍት አዳራሽ የሚመረቀውን መፅሐፍ ያዘጋጁት ወይዘሪት በቀለች ቶላ ናቸው፡፡ 128 ገፆች ያሉት መፅሐፍ በ40 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በውስጡም የጤፍ፣ የጎደሬ፣ የበቆሎ፣ እንሰት፣ የማሽላ እና የሌሎችም ሰብሎች እንጀራን አስመልክቶ ሙያዊ ማብራሪያ ይሰጥበታል፡፡ አዘጋጇ የሙያ መፅሐፍ ሲፅፍ ይህ አራተኛቸው ነው፡፡

 

 

Read 1130 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 10:47