በዚሁ ፊልም ላይ ዳንኤል ጠበቃ ሆኖ የሚተውን ሲሆን ሁለት ህፃናት በአንዲት የሙት መንፈስ ራሳቸውን እንዲገድሉ ሲገፋፉ የሚተርክ ነው፡፡በሃሪ ፖተር ፊልሞቹ እጅግ ዝነኛ የሆነው ዳንኤል ራድክሊፍ፤ ሰሞኑን 23ኛ ዓመት ልደቱን ሲያከብር “ኤፍ ዎርድ” በተባለ የሮማንቲክ ኮሜዲ እና “ሆርንስ” በተሰኘ የፋንታሲ ፊልሞች ለመተወን ስምምነት ላይ መድረሱ ይፋ ሆኗል፡፡ በትወና ሙያው 12 ዓመታት ያስቆጠረው ዳንኤል ራድክሊፍ፤ ከ11 ዓመቱ ጀምሮ በተወነባቸው ስምንት ሃሪፖተር ፊልሞች 70 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል፡፡ ባይ ዘ ነምበርስ የተባለው ድረገፅ በሰራው አሃዛዊ ስሌት፤ ዳንኤል የሃሪፖተርን ፊልሞች ጨምሮ በተወነባቸው ከሃያ የማይበልጡ ፊልሞች በዓለም ዙርያ 7.80 ቢሊዮን ዶላር ያስገባ እና በሚሰራው አንድ ፊልም በአማካይ እስከ 223.42 ሚሊዮን ዶላር ማስገኘት የሚችል ምርጥ ወጣት ተዋናይ ነው፡፡