Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 July 2012 10:33

የአውሮፓ ዋንጫው የምንግዜም ምርጥ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በኢንድያና ጆንስ ፊልሞቹ ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፈው ሃሪሰን ፎርድ 70ኛ ዓመቱን ባለፈው ሰሞን ደፈነ፡፡ የራስ ፀጉሩን ሙሉ ለሙሉ መላጨቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ አስተያየት ሰጭዎች ሃሪሰን ፎርድ በፀጉሩ ፋሽን ተወዳጅ እንደነበር ሲገልፁ መላጨቱ የሚለይበትን የትወና ውበት የሚያጠፋ ነው በሚል ተችተውታል፡፡ ሃሪሰን ፎርድ ለምን ፀጉሩን እንደተላጨ ለማወቅ እንዳልተቻለ የገለፀው የቲኤም ዜድ ዘገባ፤ ምናልባትም በቅርብ ጊዜ ቀረፃው በተጀመረ ፊልሙ ገፀባህርይ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር መላምቱን ሰንዝሯል፡፡

ከ15 መታት በፊት አንጋፋው ተዋናይ ጆሮውን ተበስቶ ሎጢ በማንጠልጠል አነጋጋሪ እንደነበር ያወሳ ሌላ ዘገባ፤ በወቅቱ ለምን ይህን ተግባር እንደፈፀመ ሲጠየቅ ከጓደኞቼ ጋር ተመሳሳይ ስልክ እና ሰዓት ነበረን፤ ከእነሱ ጋር ሙሉ ለሙሉ ለመመሳሰል ጆሮዬን ተበስቻለሁ ማለቱን አውስቷል፡፡ ሃሪሰን ፎርድ 70 ዓመት እንደሞላው  በሙያው እንደሚቀጥል ተጠይቆ፤ ጡረታ ላረጁ ሰዎች ነው የሚል ምላሽ መስጠቱን የሚገልፁ መረጃዎች፤ ባለው ልምድና በአትራፊነቱ ዘንድሮም በታላላቅ ስቱዲዮዎች ለፊልም ስራዎች እየተፈለገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ዘንድሮ በሶስት የፊልም ስራዎች ቀረፃ መጠመዱን የገለፀው ያሁ ኒውስ በበኩሉ፤ በሚቀጥለው ዓመት ለእይታ ይበቃሉ የተባሉት እነዚህ ፊልሞቹ “ኤንድለስ ጌም”፤ “ፓሮንያ” እና “42” የሚሉ ርእሶች እንዳላቸው ገልጿል፡፡  ከሆሊውድ የምንግዜም ስኬታማ እና አትራፊ ተዋናዮች አንዱ የሆነው ሃሪሰን ፎርድ፤ በትወና ሙያው 50 ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን በመሪ ተዋናይነት የሰራባቸው ፊልሞች በዓለም ዙርያ እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝዋል፡፡

 

 

 

Read 1031 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 10:37