Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 July 2012 10:26

ስፓይስ ገርልስ ኦሎምፒክን ይዘጋሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ1990ዎቹ በፖፕ ሙዚቃቸው በመላው ዓለም ተወዳጅ የነበሩት ስፓይስ ገርልስ፤ በ30ኛው ኦሎምፒያድ የመዝጊያ ስነስርዓት ዋና ኮንሰርት አቅራቢ እንደሆኑ ተገለፀ፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ የመዝጊያ ስነስርዓት በሚቀርቡ የሙዚቃ ድግሶች ዋናውን ድምቀት ይፈጥራሉ የተባሉት ስፓይስ ገርልስ ከተበታታኑ በኋላ የሙዚቃ ቡድናቸውን ለኮንሰርት ስራ ያጣመሩት ከ5 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡ በ30ኛው ኦሎምፒያድ የመዝጊያ ስነስርዓት ከስፓይስ ገርልስ ጋር ዘ ሁ፤ ጆርጅ ማይክል፤ ኒው ኦርደርና ብለር የተባሉ ሙዚቀኞችና ቡድኖች ኮንሰርቶች ያቀርባሉ፡፡

በመድረክ ላይ በሚያሳዩት አስደናቂ ትርኢትና በፋሽኖቻቸው የሚታወቁት ስፓይስ ገርልስ፤ ከኦሎምፒኩ በፊት “ቪቫ ፎርኤቨር” የተባለ ሙዚቃዊ ፊልማቸውን ለማሻሻጥ ከያሉበት ተሰባስበው ያለፈውን አንድ ዓመት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡

ስፓይስ ገርልስ በ1994 እ.ኤ.አ ላይ የተመሰረተ እና በፖፕ ሙዚቃ ዳንስና ስልቶች ለም አቀፍ እውቅና ያገኘ ቡድን ሲሆን አባላቱ ጄሪ የምትባለው ጌሪ ሃሌዌል፤ ቤሊ የምትባለው ኤማ ቢንቶን፤ ስፖርቲ የምትባለው ሜላኒ ቺሾላም፤ ስኬሪ የምትባለው ሜላኒ ብራውንና ፖሽ የምትባለው ቪክቶርያ ቤካም ናቸው፡፡

እስከ 2007 እ.ኤ.አ አራት አልበሞችን የሰራው የስፓይገርልስ ቡድን፤ በዓለም ዙርያ ከ75 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎችን በመሸጥ የተሳካለት ሲሆን በ1997 “ስፓይስዎርልድ” በሚል በሙዚቃ ቡድኑ የተሰራ ፊልም ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንዳስገኘና በኮንሰርቶች፣ በአልበም ሽያጮችና በተለያዩ የንግድ ስራዎች እስከ 800 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ስኬታማ እንደሆነ ታውቋል፡፡

 

 

Read 1463 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 10:31