Thursday, 24 September 2020 00:00

በስኮትላንድ አንዲት በግ 490 ሺህ ዶላር ተሸጠች

Written by 
Rate this item
(0 votes)


          “ደብል ዲያመንድ” የሚል ስያሜ ያላትና በአለማችን እጅግ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ በማውጣት ክብረ ወሰን ያስመዘገበችው በግ፣ ሰሞኑን ስኮትላንድ ውስጥ በተካሄደ ጨረታ በ490 ሺህ ዶላር መሸጧን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
ስኮቲሽ ናሽናል ቴክሴል በተባለው የአገሪቱ አጫራች ኩባንያ አማካይነት ላንካርድ በተባለው ከተማ በ13 ሺህ ዶላር መነሻ ዋጋ ለጨረታ የቀረበችው ይህቺው “ታሪካዊ በግ”፤ በስተመጨረሻም ባልተጠበቀ ዋጋ በ490 ሺህ ዶላር መሸጧን ዘገባው አመልክቷል፡፡
ጨረታውን ያሸነፉት ሶስት የእንስሳት እርባታ ኩባንያዎች በጋራ ባቀረቡት ዋጋ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፤ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ ክብረወሰኑን ይዛው የነበረችው እ.ኤ.አ በ2009 በ307 ሺህ ዶላር የተሸጠችው #ዴቨሮንቫሌ ፐርፌክሽን; የተሰኘች በግ እንደነበረችም አስታውሷል፡፡

Read 2962 times