Wednesday, 23 September 2020 00:00

ባራክ ኦባማ አዲስ መጽሐፍ ሊያሳትሙ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤“ኤ ፕሮሚስድ ላንድ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በመጪው ህዳር ወር መጨረሻ በገበያ ላይ እንደሚውል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ኦባማ ከወጣትነት ዘመናቸው እስከ ፕሬዚዳንትነት ያሳለፉትን ህይወትና ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ያጋጠሟቸውን ነገሮች የሚዳስሱበት ይህ የግል ማስታወሻ መጽሐፍ፤በ25 የተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለገበያ እንደሚበቃም ዘገባው አመልክቷል፡፡
ፔንጉዊን ራንደም ሃውስ በተባለው ታዋቂ አሳታሚ ኩባንያ አማካይነት ለህትመት የሚበቃው “ኤ ፕሮሚስድ ላንድ”፤ 768 ገጾች እንዳሉት የተነገረ ሲሆን፣ 45 ዶላር የመሸጫ ዋጋ እንደተተመነለትና  በሚሊዮኖች ኮፒ ይሸጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል፡፡
ኦባማ ከዚህ ቀደም “ድሪምስ ፍሮም ማይ ፋዘር” እና “ዘ ኦዳሲቲ ኦፍ ሆፕ” የተሰኙ ሁለት ተወዳጅ መጽሐፍትን ለአንባብያን ማቅረባቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

Read 2859 times