Print this page
Monday, 21 September 2020 00:00

47 ሚ. ሴቶች ወደ ከፋ ድህነት ሊገቡ እንደሚችሉ ተመድ አስጠነቀቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በመላው አለም የሚኖሩ 47 ሚሊዮን ያህል ሴቶችና ልጃገረዶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠራቸው ዘርፈ ብዙ ቀውሶች ሳቢያ ወደ ከፋ ድህነት ሊገቡ እንደሚችሉና በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለው የሃብት ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ይሰፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመድ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል፡፡
ድርጅቱ እንዳለው የሴቶች ድህነት መጠን እስከ መጪው የፈረንጆች አመት በ9.1 በመቶ ይጨምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ኮሮና ከኢኮኖሚ አንጻር ሁሉንም ተጠቂ ቢያደርግም፣ ሴቶችና ልጃገረዶች ግን በከፋ ሁኔታ ከገፈቱ ቀማሽ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በወረርሽኙ ሳቢያ ወደ ድህነት ይገባሉ ተብለው ከሚጠበቁት 96 ሚሊዮን ያህል ሰዎች መካከል 47 ሚሊዮን ያህሉ ሴቶችና ልጃገረዶች እንደሚሆኑ የገለጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም፤ ይህም በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ የአለማችን ሴቶችና ልጃገረዶችን ቁጥር ወደ 435 ሚሊዮን ከፍ እንደሚያደርገው አመልክቷል፡፡
ሴቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከስራ ገበታቸው የመፈናቀል ዕድላቸው ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር በ19 በመቶ ከፍ እንደሚል የጠቆመው ድርጅቱ፤ በብዛት ለከፋ ድህነት ከሚጋለጡት መካከልም የአፍሪካ አገራት ሴቶችና ልጃገረዶች እንደሚገኙበትም አክሎ ገልጧል፡፡


Read 3531 times
Administrator

Latest from Administrator