Saturday, 21 July 2012 12:43

“ቁንጮ” እና ቬሎ ፊልሞች ሊመረቁ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ቅዱስ ፊልም ፕሮዳክሽን ሰርቶት ዮሐንስ ተረፈ ፕሮዲዩስ ያደረገው “ቁንጮ” ኮሜዲ ድራማ ፊልም ሊመረቅ ነው፡፡ ቴዎድሮስ አበራ የፃፈውና ዮሐንስ ተረፈ ያዘጋጀው የ96 ደቂቃ ፊልም ነገ በአዲስ አበባ እና በክልል የግል እና የመንግስት ሲኒማ ቤቶች የሚመረቅ ሲሆን ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ተመርቆ መታየት ይጀምራል፡፡ በፍቅር፣ በጓደኝነት፣ በትዳርና በቤተሰብ ሕይወት ዙሪያ በሚያጠነጥነው ፊልም ላይ ዝናህ ብዙ ፀጋዬ፣ ጀምበር አሰፋ፣ ኤልያስ ወሰንየለህ፣ ብሩክታዊት ምትኩ፣ ሰላም ገብሬ፣ ሮቤል ሰሎሞን፣ ድርሻዬ ኢትዮጵያ፣ ሊሊ ወርቁ እና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

በሌላም በኩል ሐመሩሐ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን በራማ ፊልም ፕሮዳክሽን አማካይነት ያሰራውን “ቬሎ” የተሰኘ የ95 ደቂቃ የፍቅር ፊልም፣ ከነገ ጀምሮ በሌሎች ሲኒማ ቤቶች እንደሚታይና በአምባሳደር ሲኒማ ከትናንትና ጀምሮ መታየት መጀመሩን ገለፀ፡፡ በራኒ ዮሐንስ ዋቅጅራ የተደረሰው ፊልም፣ በቢኒያም ዮሐንስ ወልዴ የተዘጋጀ ሲሆን ዝግጅቱም 10 ወር ፈጅቷል፡፡ ራኒ ዮሐንስ፣ ሊዲያ ጥበቡ፣ አማን አስፋው፣ ኢየሩሳሌም ተሰማ፣ ኤልሳቤጥ ድንበሩ፣ ይታገሱ ገሥጥ ተጫኔ እና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

 

 

Read 1190 times Last modified on Saturday, 21 July 2012 12:52