Saturday, 21 July 2012 12:26

የ30ኛው ኦሎምፒያድ መክፈቻ አጓጉቷል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ከሳምንት በኋላ በለንደን ከተማ የሚጀመረው 30ኛው ኦሎምፒያድ መክፈቻ ስነስርዓት አጠቃላይ ገፅታ  በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡ የ70 አገራት መሪዎችን ጨምሮ 80ሺ ተመልካቾችን በሚያስተናገዱበት የኦሎምፒክ ስታድዬም መክፈቻው ሲደገስ እስከ 3 ሰዓት ይፈጃል ፡፡   በታዋቂው ዲያሬክተር ዳኒ ቦየል የሚዘጋጀው ስነስርዓቱ በአረንጓዴ ቀለም የሚታጀብ ነው  ተብሏል፡፡ ዳኒ ቦየል ስላምዶግ ሚሊዬነር በተባለው ፊልሙ ስምንት የኦስካር ሽልማቶችን የሰበሰበ እንግሊዛዊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የመክፈቻው ስነስርዓት  አጠቃላይ ወጪ 27 ሚሊዮን ፓውንድ ይደርሳል የተባለ ሲሆን በዓለም ዙርያ እስከ 4 ቢሊዮን ድምር ተመልካች እንደሚከታተለው ይጠበቃል፡፡

እንግሊዝን የግብርና ባህል ባንፀባረቀ ድባብ የተሟሸው ስነስርዓቱ  የኦሎምፒኩ ተሳታፊ 205 አገራት 10ሺ ልኡካንን ሰልፍ ሲታይበት በልዩ የዳንስ  ትርኢቱ ደግሞ 10ሺ በጎ ፈቃደኞች ከማሳተፉም በላይ  70 በጎች፤ 12 ፈረሶች እና 10 ዶሮዎች የትርኢቱ አካል ናቸው፡፡ አርቴፊሻል ደመና በኦሎምፒክ ስታድዬሙ ላይ ያንዣብባል፡፡ የኦሎምፒኩን መክፈቻ ከ205 ተሳታፊ አገራት 10ሺ አትሌቶች እንዲሁም 23 ሺ አልባሳትም ለትርኢቱ ይቀርባሉ፡፡የመክፈቻው ስነስርዓት በሙዚቃ ዝግጅቶችም የሚታጀብ ሲሆን ዘኪንግስ፤ ሃንድልስ የሮሊንግ ስቶንስ ባንዶችን የሚያሳትፉ ኮንሰርቶች ናቸው፡፡ የመክፈቻው ስነስርዓት መዝጊያ የሆነውን ሙዚቃ የቀድሞው ቢትልስ የሙዚቃ ባንድ አባል ፖል ማካርቲኒ እንዲጫወትም እቅድ ተይዟል፡፡

 

 

 

Read 745 times Last modified on Saturday, 21 July 2012 12:33