Saturday, 21 July 2012 12:19

ራምቦ በልጁ ሞት ተጠያቂ መባሉ ሃዘኑን የከፋ አድርጎታል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

የ66 ዓመቱ እውቅ ተዋናይ ሲልቨስተር ስታሎን  በልጁ ሞት ለተደራራቢ ሃዘኖች ተጋለጠ፡፡ ከሳምንት በፊት በመኖርያ ቤቱ ሞቶ በተገኘው ልጁ ሳጌ ስታሎን አሟሟት አባት ሲልቨስተር ስታሎን መጠየቅ አለበት በሚል ዘገባዎች እየጠወጡ ናቸው፡፡ ከ10 ቀናት በፊት የ33 ዓመቱ ሳጌ ስታሎን በሆሊውድ አቅራቢያ በሚገኘው ስቱድዮ ሲቲ መንደር በሚገኝ አፓርትመንቱ ባልታወቀ ምክንያት ሞቶ ተገኝቷል፡፡ አባቱ ሲልቨስተር ስታሎን በድንገተኛው ሁኔታ ከከፋ ሃዘን ላይ መውደቁ በተገለፀበት ዋዜማ ደግሞ ለልጁ አሟሟት ተጠያቂ ነው በሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸው ለከፍተኛ ጭንቀት እንደዳረገው የተለያዩ ዜናዎች አናፍሰዋል፡፡ በሳጌ ስታሎን አሟማት ላይ ፖሊስ ከለፍተኛ ምርምሩን እንደቀጠለ ያወሳው ዘ ሎስ አንጀለስ ታይምስ በመኖርያ ቤቱ በርካታ የመድሃኒት ብልቃጦች መገኘታቸውን በመጥቀስ ምናልባትም የሞቱ ምክንያት ከልክ ያለፈ መድሃኒት ከመውሰድ ጋር ሊያያይዝ ይችላል ብሏል፡፡

የስታሎን ቤተሰብ ቃል አቀባይ የልጁ አሟሟት በፍፁም ራስን ከማጥፋት ጋር መያያዝ እንደሌለበት ያስታወቀ ሲሆን መገናኛ ብዙሃን ባልተጣሩ መረጃዎች በሃዘን ላይ የሚገኘውን ቤተሰብ ከማስጨነቅ እንዲቆጠቡ ተማፅኗል፡፡ ቲኤምዜድ ከትናንት በስቲያ ይፋ ባደረገው መረጃ ሳጌ ስታሎን በአደገኛ መድሃኒቶች ህገወጥ ዝውውር ሳይሰራ እንደማይቀር መገመቱን ገልፃል፡፡ ሞቶ በተገኘበት መኖርያ ቤቱ በተገኙ ብልቃቶች ከ30ሺ በላይ የተለያዩ መድሃኒቶች እንክብሎች መገኘታቸው ምክንያት አድርጎ ጠቅሷል፡፡ሲልቨስተር ስታሎን ልጁ ሳጌ 14 ዓመት ሲሆነው በሮኪ 5ኛ ክፍል ፊልም የተወነ ሲሆን በ1996 እኤአ ላይ በታየው ዴይላይት የተባለ ፊልም ላይ አብረው መስራታቸውም ታውቋል፡፡

 

ሲልቨስተር ስታሎን ከወር በኋላ በዲያሬክተርነት እና በተዋናይነት ከታዋቂ የአክሽን ፊልም ኮከብ ተዋናዮች ጋር የሰራውን ዘ ኤክስፕንደብልስ ፊልም እንደሚያስመርቅ ይጠበቃል፡፡

 

 

Read 1872 times Last modified on Saturday, 21 July 2012 12:25