Saturday, 21 July 2012 12:19

ማዶና በፈረንሳይ ፖለቲከኞች ልትከሰስ ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

ማዶና  ቀኝ ዘመም ብሄራዊ ግንባር የተባለ የፈረንሳይ ፖለቲካ ፓርቲ መሪን በናዚ በመመሰል በፓሪስ ባቀረበችው ኮንሰርት ክስ ሊመሰረትባት መሆኑን ቢቢሲ ገለፀ፡፡ ኤምዲኤንኤ የተባለ 12ኛ የስቱዲዮ አልበሟን ለማስተዋወቅ ባለም ዙርያ በ65 ከተሞች ኮንሰርት የማቅረብ እቅድ ይዛ እየሰራች ነው፡፡  ከሳምንት በፊት በፓሪስ ባቀረበችው ኮንሰርት የናዚን ተግባራት በመተወን የዳንስ ትርኢቶቿን በማቅረቧ ማዶና በፈረንሳይ ፖለቲከኞች ስትተች ሰንብታለች፡፡ በፓሪሱ ኮንሰርት ላይ  ኖ ባዲ ኖውስ ሚ በተባለው ዘፈኗ የፖለቲካ ፓርቲውን ሴት መሪ ወይዘሮ ማሪን ፔለን በናዚ መስላ ትርኢቷን ማቅረቧ የትችቱ ዋና ምክንያት ነው፡፡ ይህ ተግባሯ በስም ማጥፋት የሚያስጠይቃት መሆኑን የገለፀው የፓርቲው ቃል አቀባይ  ሲሆን ሌሎች  ፖለቲከኞች በቁጣ ማዶናን በማውገዝ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

አንዳንድ ፖለቲከኞች ማዶና በፓሪስ ከተማ ከ5 ሳምንታት በኋላ በድጋሚ የምታቀርበው ኮንሰርትም እንዲሰረዝ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የ54 ዓመቷ ማዶና በዓለም ዙርያ ኤምዲኤንኤ የተባለውን አልበሟን ለማስተዋወቅ ድግሷን በእስራኤሏ ከተማ ቴልአቪቭ ማቅረብ የጀመረችው ማዶና በወቅቱ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰልምን እመኛለሁ ብላ ተናግራ ነበር፡፡ ማዶና ከዓመታት ቀደም ብሎ በዓለም ዙርያ ባቀረበችው ኮንሰርት 400 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት እንደተሳካላት ይታወሳል፡፡

 

 

 

Read 950 times Last modified on Saturday, 21 July 2012 12:25