እስከዚህም ፍቅርሽ
ከሰንደል ጭስ በላይ
ደምቆ የማይገዝፈው
ምንሽን ልፃፈው?
እስከዚህም ፍቅርሽ
በጧት የረገፈው
ከዕድሜ እሬሳ ውጭ
ዋኝታ ምኑን ታውጣው
ነብሴ ከባለፈው?
እስከዚህም ፍቅርሽ
ዘመን ያሳረጠው
ምኑን አስታውሼ
ሣጌን እየማኩኝ
እንባዬን ልዋጠው?
እስከዚህም ፍቅርሽ
ሲነድፍ ያለሰንኮፍ
መታሁ ቢልም ለኮፍ
እንኳንና ሰምበር
ስምሽስ ማን ነበር?
Saturday, 29 August 2020 15:32
እስከዚህም ፍቅርሽ
Written by (ኑረዲን ኢሳ)
Published in
የግጥም ጥግ