Saturday, 29 August 2020 11:07

‹‹...የኮሮና ወረርሽኝ ለአመታት ወደሁዋላ መልሶናል…››

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  • በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፡፡ በቤት ውስጥ በባህላዊ መንገድ ልጅን መውለድና ከዚህ ጋር በተያያዘም በሚከሰቱ የጤና ችግሮች ሞቶች እንደሚኖሩ       ይገመታል፡፡  
    • ያልታቀደ እርግዝናን ለመከላከል የሚያስችሉ መከላከያዎችን ለመው ሰድ እንዲሁም ሳይፈለግ የተጸነሰውን ጽንስ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ለማቋረጥ    የሚያስችሉትን አገልግሎቶች ለመጠቀም ሰዎች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ጤና ተቋማቱ ለመሄድ ስለማይደፍሩ ከነችግሩ በቤታቸው መታቀባቸው ውጤቱ      አስፈሪ ነው፡፡
     • በ Covid-19  ምክንያት በአለም አቀፍ ደረጃ ሚሊዮኖች ያልታቀደ እርግዝናን ለማስወገድና ያልታቀደ እርግዝናን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የእርግዝና         መከላከያዎችን ለማግኘት አልቻሉም፡፡
              ምንጭ….Guttmacher Institute

     በታዳጊ አገራት ውስጥ ያሉ ብዙ ሴቶች ዛሬም ባልታቀደ እርግዝና እንደሚቸገሩ መረጃዎች የሚያሳዩ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የስነተዋልዶ ፕሮግራም እና ጉትማቸር ኢንስቲ ቲዩት ገልጸዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ የነበረው ያልተፈለገ እርግዝና መጠኑ እየቀነሰ እንደነበር ከላይ የተጠቀሱት ድርጅቶች ገልጸዋል ፡፡ መጠኑም በ1990 በእድሜያቸው ከ15-49 ከሆኑ አንድ ሺህ ሴቶች 79 የነበረ ሲሆን በ2019 ግን ወደ 64 ዝቅ ያለ ነበር፡፡ ለዚህም የመከላከያ ዘዴዎቹን አቅርቦትና አገልግሎት በመጨመር እና ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ አለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግስታት እንዲሁም ባለሙያዎች ምስጋና ይግባቸው ተብሎአል፡፡     
ከላይ የተጠቀሰው ነገር እንዳለ ሆኖ Covid-19 ከተከሰተ ጀምሮ ምንም እንኩዋን የጤና አገልግሎቱ ያልተቋረጠ እንዲያውም በጥንቃቄ የሚተገበር ቢሆንም ብዙዎች ከቤት መውጣት አያስፈልግም የሚለውን ህግ በማክበርና ቫይረሱን በመፍራት ከማይፈልጉት የስነተዋልዶ ጤና ችግር ጋር በቤታቸው እንዲቆዩ እራሳቸውን በመወሰናቸው ምክንያት ለአደጋ መጋለጣቸው አልቀረም እንደ ጉትማቸር ኢንስቲቲዩት ማብራሪያ፡፡ በዚህም ምክንያት ቀደም ሲል ያልተፈለገ እርግዝናን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የማቋረጥንና ከእርግዝናው አስቀድሞም መከላከያውን በመውሰድ ሴቶች ለችግር እንዳይጋለጡ የሚያደርገውን አሰራር በአለም አቀፍ ደረጃ ለመቀጠል አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፡፡     
Zara Ahmed, የተባሉ በጉትማቸር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የፖሊሲ ስራ አስኪያጅ  እንደሚሉት ከሆነ Covid-19 ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል የሚያስችሉ የህክምናና የምክር አገልግሎት ስራዎችን ስለሚያቀዛቅዘውና የአገልግሎት ሰጪዎቹ ህብረተሰቡ ዘንድ ተደራሽነታቸውን በመቀ ነስ ረገድ የሚሳዩት ለውጥ እንዲሁም የተጠቃሚዎችም ወደ ጤና ተቋሙ መሄድ መቀነስ ተደ ማምሮ የጤና አገልግሎቱን ሊቀንሰው እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ Ahmed በመቀጠልም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባደረሰው አስፈሪ ሁኔታ ሳቢያ የጤና አገልግሎቱን ተግባር አስቸጋሪ ከማድረጉም ባሽገር አንዳንድ ሀገራት ለስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑትን መሰረ ታዊ ነገሮች Covid-19ን ለመከላከል እንዲያስችላቸው አቅጣጫ በመቀየራቸው ችግሩን የበለጠ ውስብስብ እንደሚያደርገው መስክረዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ April/2020 ጉትማቸር እንደተነበየው በታዳጊ አገራት አገልግሎቱ ወደ 10% የሚቀንስ ሲሆን ኮሮና ቫይረስን ለመከላል በወጣው ራስን ከቫይረሱ የመከላከል ህግ ምክንያት በቤት መቆየት የሚለው አሰራር ችግሩን ወደ 15 ሚሊዮን ተጨማሪ ያልታቀዱ እርግዝናዎች እንዲከሰቱ ምክንያት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም ውጤቱ 168,000 ተጨማሪ የጨቅላ ዎች ሞት፤28,000 ተጨማሪ የእናቶች ሞት እና ሶስት ሚሊዮን ደህንነቱ ያልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ይከሰታል ተብሎ ይገመታል፡፡
በቅርብ ጊዜ የወጣው የጉትማቸር እና ተባባሪ አካል ያደረገው ጥናት በ Lancet Global Health ታትሞ ለንባብ የቀረበው እንደሚገልጸው በታዳጊ ሀገራት ያለው ያልታቀደ እርግዝና ሶስት እጥፍ ካደጉት ሀገራት ይበልጣል፡፡ በታዳጊ ሀገራት ያሉ ሴቶች 34 ከሚሆኑ ያደጉ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ያልታቀደ እርግዝና ከ1000 ሴቶች 93/ያህል ነው፡፡
በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ በአመት ያልታቀደ እርግዝና ዝቅተኛ ቁጥር ሲሆን ከ1000 ሴቶች 35/ ያህል ነው፡፡ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ግን ከፍተኛ ሲሆን እሱም ከ1000 ሴቶች 91/ ያህል ነው፡፡  ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚኖሩ ሴቶች ከዝቅተኛው የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ተጠቃሚዎች መካከል መሆናቸውም እሙን ነው፡፡    
ጥናቱ በመጨመርም እንደሚገልጸው ያልታቀደ እርግዝና ሲከሰት ጽንስን በማቋረጥ በአለም አቀፍ ደረጃ በ1990ዓ/ም ከነበረበት 51% ከ2015-2019ዓ/ም ወደ 61% አድጎአል፡፡ ጽንስን የማቋረጥ ድርጊት ቀስ በቀስ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ባለፉት አስራ አምስት አመታት ግን መጠኑ መጨመሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሁኔታው ጽንስን ለማቋረጥ ያለው ሁኔታ አመቺ መሆኑን ወይንም ያልታቀደ እርግዝናን ለማስወገድ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡  
ያልተፈለገ እርግዝናን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ለማስወገድ አገልግሎቱን ማግኘት ባልቻሉ ሀገራት ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ድርጊቱን መፈጸማቸው ስለማይቀር ቢያንስ ቢያንስ 22,800 ሴቶች በየአመቱ ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
ሜሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል በ34 ሀገራት ያለውን አፈጻጸም በሚመለከት ባወጣው ሪፖርት የሚያሳየው እ.ኤ.አ ከ January- June ከሁለት ሚሊዮን በታች የሚሆኑ ሴቶች የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ከነበሩት ተመሳሳይ ጊዜያት እጅግ በጣም የተለየ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚገምተው በዚህ ጊዜ የተከሰተው የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ዝቅተኛ መሆን ምናልባትም ወደ 1.5 ሚሊዮን ያልተፈለገ እርግዝና በህገወጥ መንገድ እንዲ ቋረጥና 900,000 ያልታቀደ እርግዝና እንዲከሰት እንዲሁም ወደ 3,000 ሞቶችን እንደሚያስ ከትል ነው፡፡
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት COVID-19ን ለመከላከል በቤት ውስት መቆየት፤ የመጉዋጉዋዣ ሁኔታዎችን መፍራት ፤አገልግሎቱን ለፈላጊዎች የማዳረስ ችግር፤እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች የኮሮና ቫይረስን መከላከል ቅድሚያ ተሰጥቶት ለስነተዋልዶ ጤና አገል ግሎት ይውል የነበረውን አቅም ወደዚያ ማዞር፤በሕክምናው ወቅት ሊከሰት ይችላል የሚባለውን ኢንፌክሽን መፍራት…ወዘተ የመሳሰሉት የተለመደውን አሰራር እንዳይረብሹት ስጋት አለ፡፡ ከላይ የተገለጹት ምንያቶች ሁሉ ተዳምረው የብዙዎችን ህይወት የሚቀጥፈው ያልታቀደ እርግዝናን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መከላከልና አስቀድሞም መከላከል የሚያስች ለውን አገልግሎት ችላ ማለትም እንዳይኖር በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም ታዳጊ በሆኑት ሀገራት ልብ ሊባል የሚገባው ነገር መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
The International Planned Parenthood Federation (አለምአቀፉ ፕላንድ ፓረንትሁድ ፌደሬ ሽን ) እንደሚገልጸው የተወሰኑ አይነት የመከላከያ ዘዴዎች በተወሰኑ የምእራብ አፍሪካ አካባቢ ዎች ወደ 50% ያህል አቅርቦቱ ቀንሶአል፡፡ በኬንያ እንዲያውም በታዳጊነት እድሜ ላይ ያሉ ወጣቶች እርግዝና እየጨመረ ነው፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ ብዙ አመታት ወደሁዋላ መልሶናል ማለት ይቻላል ፡፡ ከዚህም የተነሳ በቤት ውስጥ በባህላዊ መንገድ መውለድና ብዙ ሞቶች እንደ ሚኖሩ ይገመ ታል  ያሉት  Diana Moreka, a coordinator of the MAMA Network ናቸው፡፡
እ.ኤ.አ በ April/2020 የተባበሩት መንግስታት አንድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል፡፡ በአለም ላይ ከ47 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ ማግኘት ሊያቅታቸው ይችላል፡፡ በአለም ላይ ወደ 7 ሚሊዮን የሚሆን ያልታቀደ እርግዝና ሊከ ሰት ይችላል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ልጃገረዶችና ሴቶች ምን ያል ቤተሰብ ሊኖራቸው እንደ ሚገባ መወሰን ወይንም ማቀድ ሊያቅታቸውና በዚህም የራሳቸውን ጤንነትና አካላቸውን መጠ በቅ ፤ኑሮአቸውንም በአቅማቸው መምራት ከማይችሉበት ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ለዚህ ግምት መነሻ የሆነውም የአለም የጤና ድርጅት ከ103 ሀገራት በደረሰው ሪፖርት መሰረት የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት በ67% ችግር እንደደረሰበትና ቀድሞ እንደነበረው መተግበር አለመቻሉ ነው፡፡     

Read 12362 times