Saturday, 29 August 2020 11:04

የጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ “ዳሳሽ መጻፎች” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ (ዶቼ ቬለ) ጋዜጠኛው ሰለሞን ሙጬ የመጀመሪያ ሥራ የሆነው “ዳሳሽ መዳፎች” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መጽሐፉ የወጣቱን ጋዜጠኛ የ30 ዓመታት የህይወት ጉዞ ከትውልድ ቀዬ እስከ እዚህ እድሜ የመጣበትን ሁኔታ ከትምህርት እስከ ሥራ ዓለም የሄደበትን መስመር በስፋትና በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ደራሲና ጋዜጠኛው የመግቢያ ጽሑፍ እውቁን የሃይማኖትና አነቃቂ ሃሳቦች ባለቤት ማይልስ ሞንሮ አባባልን ጠቅሶ ሰዎች በህይወት ያለፉበትን ልምድ ካልፃፉና ካልሰነዱ የማያውቋቸው ሰዎች ስለነሱ ይጽፉና እውነት ይጣመማል አይነት ይዘት ያለው በመሆኑ በጉብዝናው ወራት የ30 ዓመት የህይወት ጉዞውን ለዛ ባለው አገላለጽ አስፍሯል፡፡ ለግልጽነትም ብዙ ተቀኝቷል፡፡ መጽሐፉ የጋዜጠኛውን የልጅነት፣ የቤተሰብ፣ የትምህርት የስራ ሁኔታና ቦታ በስፋት የሚዳስስ ሲሆን በ319 ገጽ ተቀንብቦ በ200 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 20271 times