Print this page
Saturday, 29 August 2020 11:02

የጋዜጠኛ ስምዖን ደረጀ “ሳምጋራ” አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)


           በመጀመሪያ በዛሚ ሬዲዮ አሁን ደግሞ በብስራት 101.1 ሬዲዮ በተለይም በ “ብስራት ማለዳ” እና በአለም አቀፍ የፖለቲካ ትንታኔው ይበልጥ የምናውቀው የጋዜጠኛ ስምዖን ደረጀ “ሳም ጋራ” አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በዋናነነት በመካከለኛውና በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ መንግስታት ስልጣናቸውን ለማቆየት ሲሉ በአደባባይ ሽብርተኛ ቡድኖችን እያወገዙ በጓሮ እንዴት በድብቅ እንደሚያግዙና እንደሚያስታጥቁ በዝርዝር ያሳያል ተብሏል፡፡ የቦኮሀራሙ መሪ ቅንጡ ሜሪሴዲስ እያሽከረከረ የምዕራባውያኑን አስተምህሮ እንዴት እንደሚያወግዝ፣ አስርቱን ትዕዛዛት ለማስፈፀም መሳሪያ አንግበው ከባድ ውጊያ ስላደረጉት ቡድኖችና ለሎችም ታሪኮች በስፋት ይዳሰሳል ተብሏል፡፡
የሽብር ቡድኖች የጫካ ህይወትን ጭምር ምን እንደሚመስል የሚያስቃኘው “ሳም ጋራ” መጽሐፍ በ114 ገጽ ተቀንብቦ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 20459 times