Print this page
Tuesday, 25 August 2020 06:24

ስለ የኢትዮጵያ የፊልም ታሪክ የተፃፈው መፅሀፍ በ8 ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ሊተረጐም ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በኢትዮጵያ የፊልም ባለሙያና የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (ኢትዮ-ፊልም) መስራችና ዳይሬክተር በሆነው ይርጋሸዋ ተሾመ “A Film History in Ethiopia From Grand Palace to Ethiofest” በሚል ርእስ በእንግሊዝኛ የተፃፈው መፅሀፍ በ8 የዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ሊተረጐም ነው።
መፅሀፈ ለዚህ የታጨው በሶስት ዋና ዋና መሰረታዊ የኢትዮጵያ ፊልም ታሪኮች ላይ መሰረት አድርጐ በመፃፉና በዚህም የመጀመሪያው በሆኑ እንደሆነ አርቲስት ይርጋሸዋ ተናግሯል። ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት የመጀመያው ፊልም ማሳየት የጀመረች፣ አጭር ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራች እና “ሒሩት አባቷ ማን ነው” ከሚለው ፊልም ጀምሮ የመጀመሪያ ረጅም ፊልም ከሰሀራ በታች ካሉ አገራት ቀድማ የሰራች ስለመሆኗ የሚተነትን ነው መፅሃፉ። መፅሐፉም ከእንግሊዝኛ ወደ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ ሩስኪ፣ ስፓኒሽና ሌሎችም 8 ቋንቋዎች ሊተረጐም ተመርጧል፡፡
በ53 ገፅ የተቀነበበው መፅሃፉ በአማዞን ገበያ ላይ እየተሸጠ ይገኛለ። ፀሀፊው ይርጋሸዋ ተሾመ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫልን በማዘጋጀት የአገራችን ፊልም እድገት ላይ እያሳረፈ የሚገኘው በጐ ተፅእኖ አይዘነጋም።

Read 7254 times