Tuesday, 25 August 2020 06:13

4ኛው “ሆሄ” የስነ ፅሁፍ ሽልማት ህዳር 28 ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


           ኖርዝ ኢስት ኢቨንትስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና ከብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃህፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በየአመቱ የሚያካሂደው “ሆሄ” የስነ ፅሀፍ ሽልማት ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል። ለዚህ ውድድር የሚቀርቡ መፅሀፍት በኢትዮጵያዊያን የተፃፉ፣ በመፅሀፍ መልክ የታተሙ፣
ወጥ የፈጠራ ስራ የሆኑ፣ ግለ ታሪክ ከሆነ በባለታሪኩ በራሱ የተፃፈ መሆን እንዳለበት አዘጋጆች ገልፀዋል። ዘንድሮ አዳዲስ ተጨማሪ ዘርፎች የተካተቱ ሲሆን፣ የልጆች መፃህፍት በአማርኛ ቋንቋ ከመስከረም 1 ቀን 2011 እስከ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም፣ የልጆች መፅሀፍት በሶማሊኛ ቋንቋ ከመሰከረም 1 ቀን 2000 እስከ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፉ እንዲሁም የግጥም፣ የረጅምና የአጭር ልቦለድና የጥናትና ምርምር መጽሐፍ ከመስከረም 1 ቀን 2011 እስከ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፉ መሆን ሲኖርባቸው ግለ ታሪክ መፅሀፍ ከመስከረም 1 ቀን 2000 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፈ መሆን አለበት ተብሏል።
የተወዳዳሪ መፅሀፍት ምዝገባው ነሐሴ 25 እንደሚጠናቀቅና በዳኞች ሲገመገም ቆይቶ አሸናፊዎቹ ህዳር 28 ለሽልማት እንደሚበቁ ታውቋል።

Read 931 times