Saturday, 08 August 2020 13:11

“ትዝታሽን ለእኔ፣ ትዝታዬ ለአንቺ” በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በእሱባለው አበራ ንጉሤ የተጻፈው “ትዝታሽን ለእኔ፣ ትዝታዬ ለአንቺ” የተሰኘ ቤሳ የልብወለድ ድርሰት መጽሐፍ  ባለፈው ረቡዕ በገበያ ላይ ውሎ እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ደራሲው ከታሪክ አወቃቀር እስከ ተረክ ስልት፣ የገጸ ባሕርይ አሳሳልና አሰያየም ድረስ የራሱን አዲስ ፈርና ቴክኒክ ይዞ የመጣበትና የበኩር ስራው የሆነው ‘’ትዝታሽን ለእኔ፣ ትዝታዬ ላንቺ’’ 180 ገጾች ያሉት ሲሆን፣ በ120 ብር የመሸጫ ዋጋ በጃዕፈር መጻሕፍት እና በሁሉም መጻሕፍት አዟሪዎች እየተሸጠ ይገኛል፡፡
በማህበራዊ ድረገጾች በተለይ ስነጽሁፍ ተኮር መጣጥፎችንና ትንተናዎችን በስፋት በማጋራት የሚታወቀው እሱባለው አበራ ንጉሤ፣ አዲስ አድማስን ጨምሮ በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሄቶች ላይ ሂሳዊ ዳሰሳዎችንና መጣጥፎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡


Read 9299 times