Print this page
Saturday, 08 August 2020 12:29

ኢሠመጉ በኦሮሚያ የተፈፀሙ የሰብአዊ ጉዳቶችን እየመረመረ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፤ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከትና ግርግር በኦሮሚያ የደረሰውን የሰብአዊ ጉዳት የሚመረምር ቡድን ከሣምንቱ አጋማሽ ጀምሮ ማሠማራቱን ለአዲስ አድማስ አስታውቋል::
ተቋሙ ሁከትና ግርግር በተፈጠረባቸውና ጉዳት በደረሰባቸው ሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች የምርመራ ቡድን ማሰማራቱን አመልክቷል፡፡
በምርመራው የሚገኙ ውጤቶችን ከዓለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች አንፃር በመመዘን የተፈፀመው ድርጊት ምንድን ነው? ምን ያህል ጉዳት አጋጥሟል? መንግስት የወሰደው እርምጃስ ምንድን ነው? እነማን በድርጊቱ ተሳትፈዋል? የሚለውን የመለየት ተግባር እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

Read 8738 times