Print this page
Saturday, 01 August 2020 13:06

4ኛው “ጣና ሶሻል ሚዲያ አዋርድ” መስከረም ወር ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  “ትኩረት ለጤና ትኩረት ለጣና” በሚል መሪ ቃል በ6 ዘርፎች ሽልማት ይሰጣል

           ሶሻል ሚዲያን ለበጐ ተግባር ለእውቀትና ለአገራዊ አንድነት በበጐ መልኩ የሚጠቀሙ ተቋማትንና ግለሰቦችን የሚሸልመውና በዘመራ መልቲ ሚዲያ በየዓመቱ የሚዘጋጀው “ጣና ሶሻል ሚዲያ አዋርድ” 4ኛው ዙር መስከረም ወር ላይ አመቱን ጠብቆ ይካሄዳል፡፡
የዘመራ መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደምስ አያሌው እንደገለፁት የዘንድሮው የሽልማት ስነ ሥርዓት “ትኩረት ለጤና ትኩረት ለጣና” በሚል መሪ ቃል መስከረም ወር ላይ በ6 ዘርፎች እጩዎችን ይሸልማል፡፡
ጣና ሶሻል ሚዲያ አዋርድ ቀደም ሲል በ21 ዘርፎች ግለሰቦችንና ተቋማትን ሲሻልም እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፤ ዘንድሮ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሁሉንም ዘርፎች አካትቶ ሽልማቱን መስጠት አለመቻሉን አቶ ደምስ ገልፀዋል፡፡ ዘርፎቹም በበጐ አድራጐትና በሰብአዊነት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በጤና መረጃ ዘርፍ፣ በፈጣንና ወቅታዊ መረጃ፣ በጣና ሃይቅ አካባቢ ጥበቃና ልማት ዘርፎች ሲሆኑ፤ 6ኛው ዘርፍ ልዩ ተሸላሚ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡ በአራተኛው የጣና ሽልማት በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ጠቃሚና ማህበራዊ ፋይዳ ያለው መረጃ ሲሰጡ የነበሩና በጣና ሃይቅ ላይ በስፋት ሲሰሩ የነበሩ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፤ ጥቆማዎች ከወዲሁ እንዲላኩለት የሽልማት ድርጅቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Read 10972 times