የድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ የጋብቻ ሥነስርዓት በነገው ዕለት እንደሚከናወን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ሚካኤል በአውሮፕላን ሲጓዝ የተዋወቃትን የገልፍ ኤር የበረራ አስተናጋጅ ራሄል መኮንንን እንደሚያገባ ታውቋል፡፡ በሰርግ ስነ ስርዓቱ ላይ ጥቂት ሰዎች ብቻ እንደሚታደሙና ድምፃዊው በሰርጉ ላይ እንደሚዘፍን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ አዲስ አልበም ለማውጣት በዝግጅት ላይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡