Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 14 July 2012 11:12

“የአክሊሉ ማስታወሻዎች” ላይ ውይይት ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ በነገው ዕለት በ8 ሰዓት በአምስት ኪሎ ብሄራዊ ሙዚየም አዳራሽ “የአክሊሉ ማስታወሻዎች” በተሰኘው መፅሃፍ ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡ ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ዳይሬክተር የሆኑት ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) መሆናቸውን ጠቅሷል - ሚዩዚክ ሜይዴይ፡፡ በሌላ በኩል ቲ.ቢ.ኤም ዲጂታል ስቱዲዮ “የአዘፋፈን ጥበብ” የተሰኘ መፅሃፍና “ሙዚቃችን የሚያድገው በኛው ነው” የሚል ቪሲዲ አሳትሞ ሐምሌ 19 ቀን 2004 ዓ.ም በ10 ሰዓት በሃርመኒ ሆቴል እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡

መፅሃፉ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ብቁ ባለሙያ ለማፍራትና ድምፃውያን በተፈጥሮ ያገኙትን የድምፅ ስጦታ እንዴት ማልፀግና መንከባከብ እንደሚገባቸው የሚያስተምር ሲሆን ቪሲዲው ሳይንሳዊ የድምፅ አወጣጥና አጠባበቅን ከታዋቂና ስኬታማ ድምፃውያን ተሞክሮ ጋር በማዋሃድ የሚያቀርብና ለጀማሪዎችም ሆነ በሙያው ላሉ የሚጠቅም እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ቲ.ቢ.ኤም ዲጂታል ስቱዲዮ ለበርካታ የአማርኛ ፊልሞች አጃቢ ሙዚቃ (ሳውንድ ትራክ) በመስራት ይታወቃል፡፡

 

 

 

Read 1180 times Last modified on Saturday, 14 July 2012 11:15

Latest from