Monday, 27 July 2020 00:00

እንግሊዝ ሩስያ ክትባቴን ልትዘርፈኝ ሞክራለች አለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   አለማችን ተጨማሪ 6 ሚሊዮን ነርሶች ያስፈልጓታል ተባለ

               የእንግሊዝ የደህንነት ሚኒስትር ጄምስ ብሮከንሻየር በሩስያ መንግስት የሚደገፉ የኢንተርኔት አጭበርባሪዎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ምርምራችንን ለዘርፉ መሞከራቸውን አረጋግጠናል ሲሉ መናገራቸውን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
የእንግሊዝ የመድሃኒት ኩባንያዎችና የምርምር ቡድኖች ለኮሮና ቫይረስ ክትባትና መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የሩስያ መንግስት የደህንነት ቢሮ የሚደግፈው ኤፒቲ29 የተባለ የሩስያ የኢንተርኔት መንታፊ ቡድን የምርምር ውጤቶችን ለመዝረፍ ሙከራ ማድረጉን የደህንነት ቢሯችን ደርሶበታል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
በሌላ የጤናው ዘርፍ ዜና ደግሞ፣ በአለማችን ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በመጪዎቹ አስር አመታት ተጨማሪ 6 ሚሊዮን ያህል ነርሶችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባት ግድ እንደሚል የአለም የጤና ድርጅት ከሰሞኑ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ባወጣው አመታዊ ሪፖርቱ እንዳለው፣ እስከተጠቀሰው ጊዜ ድረስ የሚያስፈልጉትን 6 ሚሊዮን ያህል አዳዲስ ተጨማሪ ነርሶች ለማፍራት በአለማቀፍ ደረጃ በሙያው የሚመረቁ ባለሙያዎችን ቁጥር በየአመቱ በ8 በመቶ ያህል ማሳደግ ይገባል፡፡
አብዛኞቹ የአለማችን አገራት ነርሶችን በበቂ መጠን ማስተማርና ማሰልጠን ባለመቻላቸው የባለሙያዎችን እጥረት ለመቅረፍ የሌሎች አገራት ነርሶችን ቀጥረው እንደሚያሰሩ የጠቆመው ሪፖርቱ፣ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ከስምንት ነርሶች አንዷ ከተማረችበት አገር ውጭ ተቀጥራ እየሰራች እንደምትገኝም አክሎ ገልጧል፡፡


Read 9367 times