Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 July 2012 11:07

ዊልና ጃዳ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ እርዳታ ለማምጣት ቃል ገቡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የሆሊውዶቹ ኮከብ ተዋናዮች ዊል ስሚዝና ጃዳ ፒንኬት፤ ተጨማሪ እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ቃል እንደገቡ ፒፕል መጋዚን ዘገበ፡፡ በትግራይ ክልል ማጌይ በተባለች 400 ነዋሪዎች የሚገኙባት የገጠር መንደርን ከሳምንት በፊት የጎበኙት ዊልና ጃዳ፤ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴያቸውን ከ”ግሊመር ኦፍ ሆፕ” እና ከ”ሪሊፍ ሶሳይቲ ኦፍ ትግራይ” ጋር በመተባበር እያከናወኑ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ድጋፍ እንቅስቃሴ በልደት ቀናቸው 109ሺ ዶላር ገቢ ያሰባሰቡት ሁለቱ ባልና ሚስት ተዋናዮች፤ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻዎች  በማከናወን ያገኙትን ተጨማሪ 789 ሺ ዶላር ለመንደሯ ነዋሪዎች ሰሞኑን መለገሳቸው ታውቋል፡፡

በትንሿ የትግራይ ገጠር መንደር ነዋሪዎች በተደረገላቸው መስተንግዶ እና ገፀበረከቶች ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው የገለፁት ዊል ስሚዝና ጃዳ ፒንኬት፤ በትግራይ ህዝብ መደነቃቸውን፤ በጉብኝታቸው የላቀ ልምድና ተሞክሮ ማግኘታቸውንና ባዩት ሁሉ መርካታቸውን ከጉዞ መልስ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡  ተዋናዮቹ “የለው ተንደር” በተባለ መሣሪያ በገጠሯ መንደር የውሃ ጉድጓድ ሲቆፈር ተመልክተዋል፡፡ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለገጠር ነዋሪው ህይወት ምን ማለት እንደሆነ መገንዘባቸው ደስታ እንዳጐናፀፋቸው ፒፕል ማጋዚን ዘግቧል፡፡

 

Read 1137 times