Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 July 2012 11:01

የልዕልት ዲያና ፊልም ቀረፃ ተጀምሯል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሉሲ ሉ ከራስል ክሮው ጋር የኩንግኩፉ ፊልም ሠራች

በቀድሞዋ የእንግሊዝ ልእልት ዲያና የህይወት ታሪክ ላይ የሚሰራው ፊልም ቀረፃ ከሰሞኑ መጀመሩን ቢቢሲ ገለፀ፡፡ ከ15 ዓመታት በፊት በፓፓራዚዎች የሰዶ ማሳደድ ድራማ በተከሰተ የመኪና አደጋ ህይወቷ ባለፈው ልእልት ዲያና ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን ፊልም ልዕልቷን ወክላ የምትተውነው ናኦሚ ዋትስ እንደሆነች ታውቋል፡፡ በ”ትራንስፎርመርስ” ፊልም ላይ በረዳት ተዋናይነት በመስራት የተሳካላት ናኦሚ ዋትስ፤ ታላቋን ዲያና ለመተወን በመታደሌ ክብር ይሰማኛል ብላለች፡፡ ኤኮስ ፊልም የተባለ ኩባንያ የሚሰራውን ፊልም ዲያሬክት የሚያደርገው ኦሊቨር ሂርቻቢጌል ነው፡፡ የልእልቷን የመጨረሻ ሁለት ዓመታት የሚያሳዩ ፎቶዎች ተሰባስበው ለአንዳንድ የፊልሙ ትእይንቶች ቀረፃ ዝግጅት መደረጉንም ቢቢሲ አመልክቷል፡፡

“ኮውት ኢን ፍላይት” በሚል ጊዜያዊ ርእስ በሚሰራው ፊልም የልእልት ዲያና የልብ ሃኪም እና የቅርብ ወዳጇ ዶዲ አልፋይድ ገፀባህርያትም ይካተቱበታል፡፡ የፊልሙ ቀረፃ በደቡብ እንግሊዝ፤ በለንደን ከተማ ብክሮሽያ እና በሞዛምቢክ እንደሚከናወንም ታውቋል፡፡በሌላ ዜና ኪውንቲን ታረንቲኖ ዲያሬክት ባደረገው “ዘ ማን ዊዝ ዘ አይረን ፊስትስ” ፊልም ላይ ተዋናዩዋ ሉሲ ሉ ከራስል ክሮው ጋር መተወኗን ሎስአንጀለስ ታይምስ አስታወቀ፡፡ በቻርልስ ኤንጅልስ ፊልሞች ከካሜሮን ዲያዝ እና ከድሪው ባሪሞር ጋር የተወነችው ሉሲ ሉ፤ በዚህ የኩንግ ፉ ፊልም ላይ እንደሚሳካላት ዘገባው አመልክቷል፡፡ በዩኒቨርሳል ፒክቸርስ የተሰራው “ዘማን ዊዝ ዘ አየርን ፊስትስ” በሚቀጥለው ሰሞን በመላው ዓለም ይታያል፡፡

 

 

 

Read 2843 times Last modified on Saturday, 14 July 2012 11:06