Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 July 2012 10:56

ብሩስ ዊልስ የ”ዳይሃርድ” 5ኛ ክፍልን እየሰራ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ57 ዓመቱ ብሩስ ዊልስ የዳይ ሃርድን 5ኛ ክፍል መስራት መጀመሩን ሮይተርስ አስታወቀ፡፡ “ኤ ጉድ ዴይ ቱ ዳይ ሃርድ” የሚል ርእስ ያለው ፊልሙ፤ ሰሞኑን በቡዳፔስት በነበረው ቀረፃ  አንድ ባለአምስት ፎቅ ህንፃ ላይ ቃጠሎ ያደረሰ ትእይንት ተሰርቷል፡፡ ዘንድሮ ብሩስ ዊልስ “ዘ ኤክስፔንደብልስ 2” እና “ሙንራይዝኪንግደም” በተባሉ ሁለት ፊልሞች ብቻ መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ “ዳይ ሃርድ” በሚቀጥለው አመት ለእይታ እንደሚበቃ ይጠበቃል፡፡ ጆን ማክሊን የተባለ ገፀባህርይውን ብሩስ ዊልስ በብቃት መተወኑ አይቀርም ያለው ሮይተርስ፤ ፊልሙ እጅግ በተዋጣለት የአክሽን ትእይንቶቹ በገቢ ስኬት እንደሚቀዳጅም ጠቁሟል፡፡ የ”ዳይሃርድ” ፊልሞች በ1979 “ነቲንግ ላስት ፎርኤቨር” በሚል ርእስ ለህትመት በበቃ መፅሃፍ ላይ በመመስረት የተሰሩ ናቸው፡፡

“ዳይሃርድ ሊቭ ፍሪ” የተባለው የፊልሙ አራተኛ ክፍል ከአምስት ዓመታት በፊት ለእይታ ሲበቃ በዓለም ዙርያ 247 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማስገኘቱ የሚታወስ ሲሆን  ከ25 ዓመት በፊት የተሰራው የፊልሙ የመጀመርያ ክፍል 139 ሚሊዮን ዶላር፤ ከ22 ዓመታት በፊት ለእይታ የበቃው ሁለተኛው ክፍል 240 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከ17 ዓመት በፊት የታየው 4ኛው ክፍል “ዳይሃርድ ዊዝ ቬንጃንስ” 364.5 ሚሊዮን ዶላር ማስገባታቸው ታውቋል፡፡ በትወና ሙያው በቆየባቸው 25 ዓመታት ከ60 በላይ ፊልሞችን የተወነው ብሩስ ዊልስ፤ በዓለም ዙርያ 6.8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን ቦክስኦፊስ ባይነምበርስ ይጠቁማል፡፡ ብሩስ ፊልም በ”ዳይሃርድ” ላይ ለመተወን 8 ሚሊዮን ዶላር ሊከፈለው እንደሚችል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

 

 

 

Read 1451 times Last modified on Saturday, 14 July 2012 11:06