Saturday, 18 July 2020 16:47

“ማር ሲላስ እና ሌሎችም” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)


           በደራሲ አህመድ ኡስ (ሻድ) የተሰናዳውና በርካታ የአጭር አጭር ልቦለዶችን ያካተተው “ማር ሲላስና ሌሎችም” የተሰኘ የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡
ደራሲው ደራሲና ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ “ውልብታ” በተሰኘው መፅሃፉ ባስተዋዋቀው አዲስ የስነፅሁፍ ዘይቤ (የአጭር አጭር) ልቦለድ አፃፃፍ (Post cart stories) አይነት ተሰናድቶ በርካታ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍናዊና ባህላዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ፅሁፎች መካተታቸውን ደራሲው በመግቢያ ማስታወሻው አስፍሯል፡፡ በ136 ገፅ ተቀንብቦ በ75 ብር ለገበያ የቀረበው መፅሀፉ ገቢውን ሙሉ ለሙሉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሆቴል ማኔጅመንት የ3ኛ ዓመት ተማሪ ለሆነውች እና በደም ካንሰር ለተጠቃችው ወጣት ቤተልሄም ተስፋዬ ህክምና እንደሚውልም ተገልጿል፡፡
መፅሃፉን በመግዛት ወጣቷን ማገዝ ለሚፈልግ ለአስተባባሪዋ ረድኤት በ0929082876 በመደወል ማግኘት የሚቻል ሲሆን ወጣቷን ለማሳከም ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Read 29471 times