Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 July 2012 10:54

የቦሊውድ ተዋናዮች የገቢ ግብር ጭማሪ ተቃወሙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከሳምንት በፊት የህንድ መንግስት በቦሊውድ ተዋናዮች ላይ የጣለው ተጨማሪ የየገቢ ግብር ክፍያ በተዋናዮች ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የህንድ መንግስት የሆሊውድ ተዋናዮች ከሚያገኙት ገቢ ላይ 12 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ የወሰነ ሲሆን ታዋቂ ተዋናዮችና የቦሊውድ ፊልም ኢንዱስትሪ ግንባር ቀደም ተዋናዮች እርምጃውን ለእድገት አይበጅም  በሚል እየተቹት ነው፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ የህንድ ፊልሞች ገበያ እስከ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የገለፀው አርነስት ኤንድ ያንግ የተባለ ተቋም፤ በቦሊዉድ በ20 የተለያዩ ቋንቋዎች በየዓመቱ እስከ 1ሺ ፊልሞች እንደሚሰሩና ሦስት ቢሊዮን ትኬቶች እንደሚሸጡ ጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል ምርጥ ምርጥ የቦሊውድ ተዋናዮች ከሲኒማው በመራቅ በታዋቂ የቲቪ ፊልሞች ስራ ላይ ማተኮራቸውን “ዘ ሂንዱስታን ታይምስ” ዘግቧል፡፡

በገቢያቸው ከፍተኛነት እና በፊልሞቻቸው ስኬት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ከ15 በላይ ምርጥ ተዋናዮች በህንድ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚተላለፉ ድራማዎች ላይ እየተረባረቡ መሆናቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡ በህንድ የቲቪ ድራማዎች መስራት ከጀመሩ የቦሊውድ ምርጥ ተዋናዮች መካከል አሚታ ባቻን፤ ሳልማን ካሃን፤ ሻሩክ ካሃንና አኪሻ ኪማር ይጠቀሳሉ፡፡ በህንድ ከ600 በላይ ቻናሎች መኖራቸውን ያመለከተ አንድ መረጃ፤ ስርጭቶቻቸው በ100 ሚሊዮን ደንበኞች እንደተጠናከረና በየዓመቱ እስከ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚሰበሰብ ይገልፃል፡፡

 

Read 3125 times Last modified on Saturday, 14 July 2012 11:00