Saturday, 04 July 2020 00:00

“እማዬ” 1924 – 2020

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን በኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ያላቸው በአለም አቀፍ ደረጃ የተከበሩ እና የተለያዩ እውቅናዎችና ሽልማቶች የተሰጡአቸው በተጨማ ሪም በተባበሩት መንግስታት ድር ጅት የተለየ ክብርና እውቅና የተሰጣቸው የተከበሩ አውስትራሊያዊት የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት እና የፌስቱላ ህክምና ባለሙያ ነበሩ፡፡ ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ በኢትዮጵያ አስከፊውን ችግር ሲቀርፉ የኖሩ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለ60ሺህ ያህል ሴቶች የተበላሸ አካልና የጠገኑ የተበላሸ ሕይወትን መልሰው የዘሩ እውቅ የማህጸንና ጽንስ ህክምና ባለሙያ ነበሩ፡፡
‹‹የእኔ ሕልም የፊስቱላ ሕመምን ከኢ ትዮጵያ ማጥፋት ነው፡፡ በሕይወት ዘመን እያለሁ ግን ይህን ማሳካት አልችልም ፡፡ እናንተ ግን ይህን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡››
Catherine Hamlin (Dr) 1924-2020
የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር በዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈት ጥልቅ ሐዘን የተሰማው መሆኑን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፤ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ከም ንም በላይ ግን ለታካሚ ዎቻቸው መጽና ናቱን ይመኛል፡፡  
ከላይ የተመለከታችሁት ምስል እና ያነበባችሁት ምኞት የፊስቱላ ሆስፒታል መስራች የነበሩት የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ነው፡፡ የዶ/ር ሐምሊንን በሕልፈት መለየት ታካሚዎቻቸው እንዲሁም የስራ ባልደረቦቻቸው ምን ይላሉ የሚለውን ለመመልከት ለጊዜው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተ ፈጠሩ የእንቅስቃሴ ገደቦች ምክንያት አልተቻለም፡፡ በሆስፒታሉ ከታማሚዎች እና ሰራተ ኞች በስተቀር ማንም መግባት ስለማይችል ወደፊት ጊዜ ሲፈቅድ የምንመለከተው ይሆናል፡፡
የፊስቱላ ሕመም በብዙ ሴቶች ሕይወት ላይ ከባድ የስነ ተዋልዶ ጤና ችግር ሆኖ የኖረ ሲሆን የሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒ ታል በዶ/ር ካትሪን ሐምሊንና ባለቤታቸው ሬግ ሐምሊን ከተከፈተ በሁዋላ ግን ለብዙዎች ጤና እፎይታን በመስጠቱ ሐምሊንን የ60ሺህ ሴቶች እናት ለመባል አብቅቶአቸዋል፡፡ ዶ/ር ሐምሊን የዛሬ 61 አመት የወለዱትን አንድ ልጃቸውን ይዘው ወደኢትዮ ጵያ ከመጡ በሁዋላ በኢትዮጵያ ግን ለ60ሺህ ሴቶች ልዩ አገልግሎት በመስጠታቸው ታካሚዎ ቻቸውን ሴቶች የወለዱ አቸው ያህል ፍቅርና ሙገሳን የተቸሩ ሲሆን ለዚህም ከአንጀት እንዲ ደርስ እማዬ የሚል መጠሪያ ተቸረዋል፡፡  
ፊስቱላ ማለት የውስጥ አካል በተለያየ ምክንያት በመቀደድ አንዱ ከአንዱ ሲገናኝ እና የእራሱን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የማይሰጥ ሲሆን የሚኖረው ስያሜ ነው፡፡ ስለዚህም በተራዘመ ምጥና ተያያዥ ምክንያቶች ሴቶች በሚደርስባቸው የሽንት ፊኛ መቀደድ ምክንያት ሽንትን መቆጣጠር ስለሚያቅታቸው ቤተሰብ እነዚህን ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለበት መላው ሲጠፋው እንዲሄድ የሚመከረው ወደ ፊስቱላ ሆስፒታል ነው፡፡ ዛሬ ወደአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል መምጣት ብቻ ሳይሆን በቅርባቸውም አገልግሎቱን እንዲያገኙ ሁኔታዎች ተመቻችተውላቸል፡፡
የአዲስ አበባው ፌስቱላ ሆስፒታል የመጀመሪያው ይሁን እንጂ በአምስት የ ክልሎች የፌስቱላ ሕክምና የሚሰጥባቸው የተለያዩ ሆስፒታሎች ተደራጅተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆና ቸውን ይህ አምድ በተለያዩ ጊዜያት ለአንባቢ ማድረሱ አይዘነጋም፡፡
ከሆስፒታሎቹ በተጨማሪም በቅርብ ሆነው የህክምና ክትትል የሚደረግላቸው ታካሚ ዎች የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ ኑሮአቸውን በደስታ የሚኖሩበት የደስታ መንደር የሚባል ማእከል ታጠቅ ከሚባለው አካባቢ ይገኛል፡፡ ይህንን መንደርም ማስተዋወቃችን አይዘነጋም፡፡  
ካትሪን ሐምሊን ምኞታቸውን እውን ለማድረግ ይረዳሉ ተብለው ከሚታሰቡት መካክል የአዋላጅ ነርሶች ኮሌጅ አንዱ ነው፡፡ ኮሌጁ ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ ለትምህርት ከመጡባቸው የገጠር አካባቢዎች ተመልሰው በመሄድ በዚያ ያሉ ሴቶች በፊስቱላ ሕመም እንዳይያዙ ለማድረግ በቅ ርብ ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋሉ፡፡ የካትሪን ሐምሊን ምኞት ፊስቱላ ከኢትዮጵያ እንዲወገድ ነው፡፡
ይህ አምድ ለዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የማይረሳ ትዝታ አለው፡፡ የአዲስ አበባውን ፊስቱላ ሆስፒ ታል እንቅስቃሴ ለመመልከት ከስፍራው በተገኘበት ወቅት ካትሪን እድሜያቸው ከሰማንያ አመት በላይ ነበር፡፡ ነገር ግን የቀዶ ሕክምና ስራቸውን ሳያቋርጡ እየሰሩ ነበር፡፡
“When I die, this place will go on for many, many years until we have eradicated fistula altogether – until every woman in Ethiopia is assured of a safe delivery and a live baby.”
‹‹ፈስቱላ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ እስኪወገድ ድረስ….ሁሉም ሴቶች በኢትዮጵያ በጤናማ መንገድ ሕይወት ያለው ልጅ መውለድ እስኪችሉ ድረስ ይህ ስፍራ እኔ ብሞትም እንኩዋን ለብዙ አመታት ስራውን ይቀጥላል፡፡››
ዶ/ር ካትሪን ሐማሊን ፡፡  
“እማዬ “ የሚለው ስያሜ ለአንዲት ወላጅ እናት ከምትወደው ልጅዋ በመጠሪያነት የሚሰጣት ስያሜ ነው፡፡
የ96 አመት የእድሜ ባለጸጋዋን ዶ/ር ሐምሊንን በሆስፒታሎቹ ውስጥ ታካሚዎቹም ሆኑ ሰራተኞቹ ሁሉም አንቺ ብለው ነው የሚጠሩአቸው፡፡ በእንግድነት የመጣ ሰውም ቢሆን በዚያው መልክ እንዲመለከታቸው ይፈልጋሉ፡፡ የዚህ አምድ አዘጋጅ በተደጋጋሚ እንደታ ዘበችው መላው ሰራተኛ በአንድ አይነት ስሜት ለካትሪን ሐምሊን እውነተኛ ፍቅርን ነበር የሚሰጡአቸው፡፡ በሀገራችን አንዳንድ ጊዜ በሙያ ምክንያት የሚሰጥ አጠራር ቢሆንም በአ ብዛኛው ግን አንተ እና አንቺ በጣም ለሚያፈቅሩት ሰው የሚሰጥ አቀራረብ ነው፡፡
እ.ኤ.አ ከ1924-2020 ድረስ በሕይወት የቆዩት አውስትራሊያዊቷ ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን እማዬ የተባሉት ከወላጅ እናትነት በላይ በታካሚዎቻቸውና በመላ በሆስፒታሉ ሰራተኞች እናትነታ ቸው የማያጠራጥር በመሆኑ ነው፡፡ ይህ አምድ ስድስቱን የፌስቱላ ሆስፒታሎች ማለትም የአዲስ አበባውን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ዞሮ በተመለከተበት ወቅት የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ፍቅር ምን ያህል እንደነበር ታዝቦአል፡፡
“To say Catherine was a remarkable woman is an understatement. In our eyes, she was a saint,”
Carolyn Hardy, Chief Executive Officer of Catherine Hamlin Fistula Foundation
ካትሪን የተከበሩ ባለሙያ ናቸው የሚለው አባባል በእኛ እይታ ያንሳቸዋል፡፡ ካትሪን “ቅድስት” ናቸው ብንል እንወዳለን፡፡
ካሮሊን ሐንዲ
እ.ኤ.አ በ1924 ዓ/ም በሲድኒ ከተማ የተወለዱት ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ረቡእ ማርች 18/2020 በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በሚወዱዋቸው ሰራተኞቻቸውና ታካሚዎቻቸው መካከል በክብር አልፈዋል:: የክብር ዜግነት ባገኙባት ኢትዮጵያም የቀብር ስርአታቸው ተፈጽሞአል፡፡
ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን እንደምኞታቸው የፊስቱላ ሕመም ከኢትዮጵያ የሚወገድበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር እምነት ነው፡፡  


Read 4672 times