Saturday, 20 June 2020 12:00

“ካራ ማዞቭ” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የእውቁ ሩሲያዊ ደራሲ ፊዮዶር ዶስቶቪስኪ የመጨረሻ ሥራ የሆነውና “The karamazov Brothers” በሚል ርዕስ ተፅፎ ተወዳጅነትን ያተረፈው ረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ በተርጓሚ መክብብ አበበ “ካራማዞቭ” በሚል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ሰሞኑን ለንባብ በቃ።
በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተሰናዳውና በርካታ ታሪኮችን የያዘው መጽሐፉ፤ በ522 ገፆች የተቀነበበ ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ሲሆን በ300 ብር ለገበያ ቀርቧል።
ዶስቶቭስኪ በተጨማሪም “The House of the Dead” “Notes from underground” “Crime and Punishment” በሚሉና ሌሎች ሥራዎቹም ይታወቃል፡፡ ተርጓሚው መክብብ አበበ፤ ከዚህ ቀደም “ሰውና ሀሳቡ”፣ “ሕይወት በጠንቋይ ቤት” (እውነተኛ ታሪክ)፣ “የሚያቄለው ሰው ህልም”፣ ለሕጻናት የተሰናዱት “ብስክሌቷ” እና “ትንሿ ውሻ” የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል።


Read 38864 times