Saturday, 13 June 2020 11:02

“ሄሎ ታክሲ” የትራንስፖርት ገበያውን ተቀላቀለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(12 votes)

በኮቪድ 19 ሳቢያ መጨናነቅ ባሉባቸው አካባቢዎች በነፃ አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል
                      
               “ሄሎ ታክሲ” ከሰሞኑ የትራንስፖርት ገበያውን መቀላቀሉንና በ40 ተሽከርካሪዎች ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። በ50 ሚ.ብር ካፒታል እንደተመሰረተ የሚነገርለት የትራንስፖርት ኩባንያው በቀጣይ 3000 አውቶ ሞቢሎችን ከውጪ በማስመጣትና 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ለሚከፍሉ ቀሪውን 70 በመቶ በአምስት አመት ከፍለው እንዲጨርሱ ከአቢሲኒያ ባንክ ብድር ማመቻቸቱንም የድርጅቱ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወጣት ዳንኤል ዮሐንስ አስታውቋል።
ድርጅቱ ባለፈው ሰኞ በሸራተን አዲስ የታክሲ አገልግሎት መጀመሩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ አሁን ካዘጋጃቸው 250 መኪኖች ውስጥ 40ዎቹ በዕለቱ ለዢዎቹ ተሰጥተው ሥራ መጀመራቸውን ጠቁሞ ሁለተኛ ዙር ሽያጭ መጀመሩንም አስታውቋል። ይህንን ሥራ ለማሳደግና በትራንስፖርት ዘርፉ ውስጥ ሰብሮ ለመግባት ከአቢሲንያ ባንክ በተጨማሪ ከአክሎክ ጀነራል ሞተርስ ጋር በመተባበር ባለ ሰባት መቀመጫ “ዊሊንግ” የተሰኙ ዘመናዊ መኪናዎችን በሀገር ውስጥ እያስገጣጠመ ሲሆን ከእነዚሁ መኪናዎች የመጀመሪያ ዙር ለገበያ ማቀረቡን አቶ ዳንኤል ተናግሯል።
ለዘመናት ሕዝብን በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት የላዳ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ቅድሚያ የሚያገኙ ሲሆኑ ሴቶችም በዚህ ዘርፍ ለመሰማራት ተከሳሽነት ካላቸው ከ30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያውም እገዛ ተደርጎላቸው እንደሚሰማሩ ለማወቅ ተችሏል ለሙስሊም ወንድምና እህቶች በሸሪአ ህጉ መሰረት፤ ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመነጋገር፣ ከወለድ ነፃ የብድር አገልግሎት መዘጋጀቱንም አቶ ዳንኤል በመግለጫው አብራርተዋል።


Read 6266 times