Saturday, 06 June 2020 14:14

ስለ የወር አበባ መቋረጥ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  በተፈጥሮ  አንዲት ሴት በታዳጊነት እድሜዋ መፍሰስ የሚጀምረው የወር አበባ ከአመታት በሁዋላ ይቋረጣል፡፡ ይህም በእንግሊዝኛው Menopause በአማርኛው ደግሞ የወር አበባ መቋረጥ ይባላል፡፡ የወር አበባ መቼ ይቋረጣል፤መቋረጡን እንዴት ማወቅ ይቻላል፤ የወር አበባ በመቋረጡ ምክንያት ሴቶች ምን የተለየ ነገር ያያሉ፤ የሚለውን ነገር ሁሉም ሴቶች ሊያውቁት ይገባል የሚለውን ለንባብ ያሉት Debra Rose Wilson, PhD ናቸው፡፡
ይህ መረጃ የተዘጋጀው በጥያቄና መልስ መልክ ቀለል ባለ አጻጻፍ ሲሆን ታነቡት ዘንድ ወደአማርኛ መልሰነዋል፡፡ የምናስቀድመው የወር አበባ መቋረጥ ወይንም Menopause ምን እንደሆነ የተሰጠውን ትርጉም ይሆናል፡፡
የወር አበባ መቋረጥ(Menopause)ምንድነው?
ሴቶች እድሜአቸው ከፍ ሲል ማለትም ከ40-50 በሚደርስበት ጊዜ የወር አበባቸው ይቋረጣል፡፡ በእርግጥ ትንሽ ቢሆንም አንዳንድ ሴቶች እድሜአቸው 40/አመት ሳይደርስም የወር አበባቸው ሊቋረጥ ይችላል፡፡እድሜያቸው ሳይደርስ የወር አበባቸው የሚቋረጥ ሴቶች የሚያጤሱ እና በሕክምና ምክንያት ከሚወስዱዋቸው አንዳንድ ሕክምናዎች የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዲት ሴት በተከታታይ ለአንድ አመት ያህል የወር አበባ ሳታይ ከቀረች የወር አበባዋ ተቋረጠ ይባላል፡፡
የወር አበባ መቋረጥ በሰውነት ላይ አንዳንድ ለውጦችን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ለውጦች የሚባሉ ትም በድንገት የሚሰማ ሙቀት ያለው ላብ ማላብ፤ክብደት መጨመር፤የብልት መድረቅ የመሳ ሰሉት ቀደም ሲል ከነበረው የተለየ ነገር ያጋጥማል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያትም በሰውነት ውስጥ ይመረት የነበረው ኢስትሮጂን እና ፕሮጀስትሮን የሚባለው ንጥረ ነገር በወር አበባ መቋረጥ ወቅት መመረቱ ስለሚቀንስ ነው::
ሴት ልጅ እድሜዋ ከወር አበባ መቋረጥ ሲደርስ የአጥንት መሳሳት ችግርን ሊያስከትልባት ይችላል፡፡ ማንኛዋም ሴት ከዚህ እድሜ ከመድረስዋ በፊት ጠንቅቃ ማወቅና ተገቢውን የባለሙያ ምክር ማግኘት አለባት:: ባጠቃላይም በወር አበባ መቋረጥ ወቅት ለሚከሰቱ የሰውነት ለውጦች በተፈጥሮአዊ መንገድ ማለትም በአመጋገብ፤በአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመሳሰሉት ሁሉ እራስን ዝግጁ ማድረግ ይገባል::
ከዚህ ቀጥሎ የተጻፉትን ነጥቦች ማንኛዋም ሴት አስቀድማ ማወቅ ይጠቅ ማታል፡፡  
menopause በሜኖፖዝና Perimenopause ከሜኖፖዝ አስቀድሞ ባለው ሁኔታ ልዩነቱ ምንድነው?
Perimenopause ከሜኖፖዝ አስቀድሞ የሚባለው ጊዜ ልክ የወር አበባ ለመቋረጥ በተቃረበበት ወቅት ያለ ጊዜ ነው፡፡ የወር አበባ ከመቋረጡ አስቀድሞ ያለው ጊዜ ሰውነት ለሽግግር የሚዘጋጅበት እና የሚፈጠሩት ሆርሞኖች መቀነስን የሚጀምሩበት ጊዜ ነው፡፡ የወር አበባም ሙሉ በሙሉ ሳይቆም የመምጫውን ጊዜ የሚያዛባበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ትንሽ ከቆየ በሁዋላ የወር አበባው ለአንድ አመት ሙሉ በሙሉ ሳይፈስ ከቆየ የወር አበባ ተቋረጠ ይባላል፡፡
ኢስትሮጂን የተባለው ንጥረ ነገር መመረቱን በመቀነሱ ምክንያት በሰውነት ላይ የሚታየው ምልክት ምንድነው?
ይህ ሁኔታ በሚያጋጥምበት ወቅት ወደ 75%የሚሆኑት ሴቶች ሙቀትና ላብ ማላብ ይሰማቸዋል፡፡ ይህም የሚከሰተው በመኝታ ወቅት ወይንም ቀን ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ሴቶች arthralgia የተሰኘው የጡንቻ እና የመገጣጠሚያ አካላት ሕመም ወይንም የስሜት መለዋወጥ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ በእርግጥ ይህ የጤና ሁኔታ በሆርሞን መቀነስ፤ወይም በሕይወት ውስጥ በሚኖሩ አንዳንድ ገጠመኞች አለዚያም በእድሜ በመግፋት ምክንያት መሆን አለመሆኑን በትክክል መናገር ያስቸግራል፡፡
ላብ ማላብና ሙቀት እንዳለ ማሳያዎቹ ምንድናቸው?
ሙቀት እና ላብ ማላብ ሲጀምር የሰውነት ሙቀት ከፍ ይላል፡፡ ይህ በሰውነት ውጫዊ አካል ላይ የተወሰነ ጉዳት ሊያስከትልበት ይችላል፡፡ ቆዳ ከለሩን ሊለውጥ ወይንም በፊት ላይ እንደ መበለዝ አይነት አንዳንድ ምልክቶችን ሊተው ይችላል፡፡ የልብ ምትን ማፋጠን ፤መጨነቅን፤ መደበርን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሲያበቃ ግን ቅዝቃዜ ሊሰማ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሴቶች የሚያደርጉዋቸውን ነገሮች ከተቆጣጠሩ ትኩሳትና ላብ የሚቀንስበት ሁኔታ ይስተዋላል:: ለምሳሌም፤-
አልኮሆል እና እንደቡና የመሳሰሉ ነገሮችን መቀነስ፤
ቅመም የበዛባቸው ፤የሚያቃጥል ምግብን መመገብን መቀነስ፤
ጭንቀትን ማስወገድ፤
ሙቀት ያለበት አካባቢ አለመሆን፤
ከልክ በላይ መወፈር እና ሲጋራ ማጤስን ማቆም፤ የመሳሰሉተ ነገሮች ላብና ሙቀቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
ሙቀቱንም ለመቆጣጠር፤-
አለባበስን ሳሳ ያለ ነገር ላይ እንደ ኮት የመሳሰሉ ነገሮችን በመደረብ ሙቀቱ ሲመጣ ለማውለቅና አየር ለማግኘት ይረዳል፡፡
በተለያዩ መንገዶች ማለትም እንደ አየር መስጫ (fan) ወይንም በእጅ የሚያዝ እና የሚውለበለብ አየር መስጫ ባሉበት ሁሉ እንዲጠቀሙበት ይዘው መንቀሳቀስ ይጠ ቅማል፡፡
ድንገተኛ ሙቀት እና ላብ በሚሰማበት ጊዜ አየር በማስወጣት እና በማስገባት ስሜቱን ለመቀነስ መለማመድ ጠቅማል፡፡
ድንገት የሚከሰተው ሙቀትና ላብ የሚያስከትውን የስሜት መረበሽ መቆጣጠር የሚያቅት ከሆነ ወደሕክምና ባለሙያ መሄድ ጠቃሚ ነው፡፡
የወር አበባ መቋረጥ menopause እንዴት አጥንትን ይጎዳል?  
የወር አበባ መቋረጥ ሲከሰት ኢስትሮጂን የተሰኘው ንጥረ ነገር መመረቱን ስለሚቀንስ እና ይህ ደግሞ በአጥንት ውስጥ ካልሲየም የሚባለው ንጥረ ነገር እንዳይኖር ስለሚያደርግ አጥንት እንዲጎዳ ምክንያት ይሆናል፡፡ አጥንት ካልሲየም ካላገኘ መጠኑን እና ሊኖረው የሚገባውን ጥንካሬ እንዲቀንስ ይገደዳል፡፡
በዚህም ምክንያት የአጥንት መሳሳት osteoporosis የተባለው የአጥንት ሕመም ይከሰታል፡፡ በዚህም ምክንያት በጀርባ አጥንት እና በሌሎች አካባቢዎች ላይ ጉዳትን ሊያስከትል፤ መጉበጥን ሊያመጣ ይችላል፡፡ አጥንት ጤናማ ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ፤
ካልሲየም ያላቸውን የወተት ተዋጽኦዎች ወይንም ጥቁር አረንጉዋዴ ቅጠላ ቅጠሎችን መመገብ፤
የቫይታሚን ዲ ተዋጽኦ ያላቸውን ምግቦች መውሰድ፤
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤
አልኮሆል መቀነስ ፤
ማጤስን ማስወገድ ….ወዘተ የመሳሰሉት ጠቃሚዎች ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የህክምና ባለሙያን ማማከር እና አጥንት ጤናማ ሆኖ እንዲቆይ መሞከር ተገቢ ይሆናል፡፡


Read 10206 times