Saturday, 06 June 2020 14:08

”በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ መሆን አልቻልንም”

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    የወረርሽኙን ጉዳት ለመቀነስ መንግስት ባስተላለፈው የምህረትና የግብር አከፋፈል ውሳኔ እንዳንጠቀም ተደርገናል ሲሉ ግብር ከፋዮች ቅሬታ አቀረቡ፡፡ “ተለዋጭ መመሪያ መጥቷል“፤ ”ወረፋ ሳይደርሳችሁ ቀነ-ገደቡ አልፏል” በሚል ሳይስተናገዱ መቅረታቸውን ተናግረዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎች በበኩላቸው፤ “አብዛኛውን ግብር ከፋይ ለማስተናገድ ችለናል፡፡ በወረፋ ያልደረሳቸው ቢኖሩም፣ የመመሪያው ገደብ ስለደረሰ ምንም ማድረግ አልቻልንም” ብለዋል፡፡ እስከ 2007 ዓ.ም ውዝፍ የግብር ዕዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች፣ ሙሉ በሙሉ ምህረት እንደተደረገላቸው፣ ከ2007 ወዲህ ያለው ደግሞ ዕዳና መቀጫ ተነስቶላቸው በሁለት የግብር የአከፋፈል መንገድ  እንዲስተናገዱ መንግስት እንደወሰነ ያስታውሳሉ - ቅሬታ አቅራቢዎቹ፡፡  
በአንደኛው መንገድ  ያለባቸውን ውዝፍ  ግብር በአንድ ወር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከከፈሉ፣ ከቅጣትና ወለዱ ምህረት በተጨማሪ፣ ከፍሬ ግብሩ ላይ የ10 በመቶ ቅናሽ ማግኘት ይችላሉ፡፡  የውዝፍ ግብር 90 በመቶ የመክፈል አቅም ካላቸው ከዕዳ ነጻ ይሆናሉ፡፡ አቅም ለሚያጥራቸው ደግሞ ሌላ የአከፋፈል አማራጭ ተሰጥቷል፡፡ ቅጣትና ወለድ ተሰርዞላቸው፣  ካለባቸው ውዝፍ ግብር ውስጥ 25 በመቶ ያህሉን በአንድ ወር፣ ቀሪውን በአንድ ዓመት ከፍለው እንዲያጠናቅቁ ዕድል የሚሰጥ ነው - የመንግስት ውሳኔ፡፡
በርካታ ግብር ከፋዮችና የገቢዎች ሚኒስቴር ሃላፊዎች እንደሚናገሩት፤ ሁለቱ
የአከፋፈል አማራጮች ሥራ ላይ ውለው፣ በርካታ ከፋዮች ተስተናግደዋል፡፡ የክፍያ ሂደት ለማጠናቀቅና ሥራውን ለማሳለጥ፣ ከኮረና ወረርሽኝ ፈተና ጋር የጊዜ እጥረት ቢያጋጥምም ሌላ ችግር አልነበረም፤ በርካታ ግብር ከፋዮች ከተስተናገዱ በኋላ ነው፤ አዲስ ችግር የተፈጠረው፡፡ 25 በመቶ የከፈሉ ቀሪውን በዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ የተፈቀደላቸው ግብር ከፋዮች እንደገና እየተጠሩ 100 ፐርሰንት መክፈል አለባችሁ ተብለዋል፡፡ ከወር በፊት የግብር ውሳኔ የተሰጣቸው ሰዎች 25 በመቶ መክፈል ይችላሉ፤ከወር በኋላ ግን አይፈቀድላቸውም ተብለዋል፡፡ ውዝፍ ግብር ባለባቸው ሁለት ሰዎች መካከል እንዲህ ያለ ልዩነት መደረጉ ግራ እንዳጋባቸው ገልጸዋል - ቅሬታ አቅራቢዎቹ፡፡
የቅሬታ አቅራቢዎቹን አቤቱታ በሚመለከት ገቢዎች መስሪያ ቤትን ጠይቀን በሰጡን ምላሽ፤ በምህረት ውሳኔ ተጠቃሚ ለመሆን የመጡ አብዛኞቹን  ግብር ከፋዮች በተገቢው መንገድ አስተናግደናል ብሏል፡፡  
የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ብርቱካን ግርማ፤ የውዝፍ ግብር ክፍያ በአንድ ጊዜ ለፈፀሙ ግብር ከፋዮች 10 በመቶ ቅናሽ እየተደረገላቸው እንደተስተናገዱ ገልጸዋል፡፡  እንደውም ከዕዳ ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት መስጠት ጀምረን ነበር ያሉት ሃላፊዋ፤ በመጨረሻዎቹ ቀናት ተስተናጋጁ---  ጠቅሰዋል፡፡
25 በመቶውን ቅድሚያ ከፍለው ቀሪውን 75 በመቶም በአንድ ዓመት ውስጥ ለ፣ጠናቀቅ የሚፈልጉ ግብር ከፋዮች በርካታዎቹ ተስተናግደዋል ብለዋል፡፡
ደንበኞችም በተቀመጠው ቀነ ገደብ መስተናገዳቸውን ሀላፊዋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ግብር ከፋዮች የምህረት እድሉን በጊዜ እንዲጠቀሙ የገቢዎች ሚ/ር በተለያዩ መንገዶች እንዳሳወቀ ሃላፊዋ ጠቅሰው፤ የአብዛኛው ሰው የክፍያ ሂደት እስከ መመሪያዎቹ ቀነ ገደብ  እንደቆዩ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻዎቹ ቀናት ብዙ ሰው ስለመጣ በሰራተኞች ላይ ጫና መፈጠሩን ሀላፊዋ ገልፀው፤ በእድሉ ያልተጠቀሙና የተመለሱ ግብር ከፋዮች ቅሬታ ሊያቀርቡ ይችላሉ:: የገቢዎች ሚኒስቴር ሳይሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ በመሆኑ በሰዓቱ ካልከፈሉ ቅጣቱም ወለዱም አይነሳም፤ሁሉንም ይከፍላሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከወር በፊት የግብር ክፍያ ተሰጥቷቸው ሳይከፍሉ የቆዩ ግብር ከፋዮች በምህረት አዋጁ መሰረት 25 በመቶውን ከፍለው፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ቀሪውን 75 በመቶ ከፍለውመጨረስ ይችላሉ፡፡ ከወር ወዲህ የግብር ውሳኔ የተሰጣቸው ግን መቶ ፐርሰንት ነው እንዲከፍሉና በዚህ መንገድ እንድናስተናግድ ነው መመሪያው የወጣወው ብለዋል፡፡


Read 8458 times