Saturday, 30 May 2020 14:26

ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ እና ጉዳቱ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

  በአለማችን በየአመቱ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ እድሜአቸው ከ15-19 የሚደርሱ ልጃገረዶች ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ እንደሚያደርጉ የአለም የጤና ድርጅት በ2020/ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ መረጃው በማከልም ከሁሉም እርግ ዝናዎች 25 % ያህሉ ሆን ተብሎ በ (induced  abortion) ይቋረጣሉ፡፡   
ማንኛዋም ሴት በነጻነት እና ኃላፊነት በተሞላው ሰብአዊ መብትዋ ምን ያህል ልጅ፤በምን ያህል የጊዜ እርቀት መውለድ እንዳለባት መወሰን ትችላለች:: ማንኛዋም ሴት በትዳር አጋርዋም ይሁን በማንኛውም ቤተሰብዋ ሳትገደድ ወይንም ተጽእኖ ሳይደርስባት በስነ ተዋልዶ ጤና ጉዳይ መረጃው እና ለአፈጻጸሙ ብቃት ኖሮአት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማድረግ የመወሰን መብት አላት፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ምንም ጉዳት ሳያስከትል በጤናማ ሁኔታ ደህንነቱ በተጠበቀ መን ገድ ለመፈጸም ህጋዊ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጽንስን ማቋረጥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በጤና ተቋምና በሰለጠነ ባለሙያ አማካኝነት ምክንያቱ አሳማኝ በሆነ መንገድ እንዲ ቋረጥ ለማድረግ በኢትዮጵያም ሕግ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ በአለም ላይ እንደሚታየው እውነታ ከሆነ ከአራቱ አንዱ እርግዝና ይቋረጣል፡፡ ጽንስን ማቋረጥ የተለያዩ ድጋፎችን ማለትም በተ ለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት በራሱ ጊዜ የሚቋረጥም ሆነ በፍላጎት እንዲቋረጥ ሲደረግ የህክ ምና አገልግሎትን መሻቱ እሙን ነው፡፡ ህጋዊ ባልሆኑ ቦታዎችና ባልሰለጠኑ ሰዎች አማካኝነት የሚሰጡ ህጋዊ ያልሆኑ ጽንስን የማቋረጥ ሕገወጥ አገልግሎቶች በታካሚዋ ሴት ላይ የሚያደ ርሱት የኢንፌክሽንና የተለያዩ የጤና ችግሮች ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ሕክምናን ይሻሉ፡፡
WHO በሚያወጣቸው መመሪያዎች እና አሰራሮች መሰረት በጤና ተቋም እና በሰለጠነ ባለሙያ አማካኝነት የጽንስ ማቋረጥ የሚከናወን ከሆነ የሴትየዋም ደህንነት ተጠብቆ የህክምና አገልግሎ ቱም አለአግባብ ሳይባክን በቀላሉ ይፈጸማል፡፡ በዘመኑ የጽንስ ማቋረጥ በመድሀኒት እንዲሆንም ይመከራል፡፡ ይሄ ሁሉ ሊሆን የሚችለው ግን በሰለጠነ የሰው ኃይልና በጤና ተቋም ሲፈጸም ነው፡፡  
ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ሲባል እርግዝናው ምንም እውቀት በሌላቸው ሰዎች ሲፈጸም እና ድርጊቱን የሚፈጽሙበት ቦታም ደረጃውን ያልጠበቀና ምቹ ያልሆነ እንዲሁም ለጤና አስጊ፤ ለኢንፌክሽን አጋላጭ ሲሆን ነው:: ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ሙያውን በማያውቁ ሰዎች ሲፈጸም የተለያዩ ባእድ ነገሮችን ማለትም እንደ ስራስር ፤በህክምናው አለም ከሰውነት ውስጥ የሽንት መቀበያ ካቴቴር…ወዘተ የመሳሰሉትን በማህጸን በኩል በማስገባት ሙያዊ ባልሆነ መንገድ የተዘጋውን የማህጸን በር ለመክፈት ትግል ማድረግና ሲሳካላቸውም አልፈው ጽንሰን ከተቀመጠበት ቦታ እየወጋጉ በመረበሽ እንዲደማና እንዲወርድ የማድረግ ስራን ይሰራሉ፡፡ ይህ እጅግ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ድርጊት ጎጂ በሆኑ ነገሮች የሚከናወን ሲሆን ውጤቱም ጽንሱ በትክክል ይቋረጥ ወይንም አይቋረጥ ለማወቅም ይሁን ተከትሎ የሚመጣውን ህመም ለማስወገድ ሲባል ወደሆስፒታል መሄድ ግድ ይሆናል፡፡ ሴትየዋ እድለኛ ከሆነች ብቻ… ያውም ለወደፊትም የምታስታምመው ቁስለት ይዛ የምትቀር ሲሆን እድለኛ ያልሆነችው ግን የማህጸን መተርተር እና ሞት ሊያጋጥማት ይችላል፡፡
በአለማችን ሴቶች፤ ታዳጊዎችን ጨምሮ ባልተፈለገ እርግዝና ምክንያት ብዙውን ጊዜ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ማከናወን አቅማችን አይፈቅድም በሚል የሚያመሩት ደህንነቱ ወደ አልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ይሆናል:: ደህንቱ የተጠበቀ ጽንስን ማቋረጥ በየሀገራቱ ህግ የየራሱ ጥያቄ ስላለውም ያንንም ማሟላት አንችልም ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌም፤-
በወጣው ህግ ላይ ጽንሱን ማቋረጥ ያስፈለገበት ምክንያት መገለጽ ይኖርበታል፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት አለመቻል ወይንም ምቹ የሆነ አገልግሎት አለመኖሩ፤
ገንዘብ የሚያስወጣ ከሆነ፤
በሰዎች ዘንድ መሳለቂያ ላለመሆን መሸሽ መደበቅ ወይንም ማፈር፤
በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ግልጽ የሆነና ጥንቃቄ የተሞላውን አሰራር አለመውደድ ወይንም በግላቸው በምስጢር መስተናገድ አለመቻላቸውን በመጥላት፤
አላስፈላጊ የሆኑ መመዘኛዎች፤ ለምሳሌም በጤና ተቋሙ የመቆያ ጊዜ፤ የምክር አገልግሎት ለማግኘት መቆየት፤ አገልግቱን ለማግኘት ሌላ ሶስተኛ ሰው ማግኘት፤ አላስፈላጊ ምርመራዎች አገልግሎቱን ቶሎ ለማግኘት አያስችሉም ብለው ስለሚ ያምኑ….ወዘተ ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ወደሚያደርጉበት ቦታ አይሄዱም፡፡
WHO ጤናን እንደሚገልጸው…ሙሉ የሰውነት አካል፤ የውስጥ አካላትን፤ የስነተዋልዶ አካላትን ጨምሮ የአእምሮ እና ማህበራዊ ደህንነት ካለምንም እውክታ ተፈጥሮአዊ ግዳጃቸውን በሚገባ እንዲወጡ በምንም ሕመም ሳይጎዱ መቆየት ነው፡፡  
ጽንስን ከማቋረጥ ጋር በተያያዘ የጤና ሁኔታ የሚመዘነው ድርጊቱ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ነው? ወይንስ? በሚለው ነው፡፡ እርግዝናው እንዲቋረጥ የተደረገው ሙያው ወይንም እውቀቱ በሌለው ሰው ከሆነ፤ እንዲሁም ድርጊቱ የተፈጸመበት አካባቢ ለበሽታ የሚያጋልጥ ከሆነ፤ አገል ግሎቱ በተሰጣት ሴት ላይ የስነልቡና ጫና፤ አግባብነት የሌለው የገንዘብ ወጪ፤ ስለሚያስከትል ይህም… ለራስዋ፤ ለቤተሰብዋ፤ እንዲሁም ቀረቤታ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ስሜትን የሚጎዳ ይሆናል:: ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስን ማቋረጥ ለደም መፍሰስ፤ ለኢንፌክሽን፤ በማህጸን በር…በብልት…በማህጸን ላይ ሕመም እንዲሰማት ያደርጋታል፡፡ ከዚህም በላይ  የጽንስ ማቋ ረጥን በህገወጥ መንገድ የምታደርግ ሴት ለሕይወት ዘመን የሚቆይ ሁልጊዜ ሕክምና የሚ ፈልግ የጤና ችግር ያስከትልባታል:: አንዲት ሴት በተደጋጋሚ ደህንነቱ ያልተ ጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ የምታደርግ ከሆነ መጨረሻው ሞት ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻ ላል፡፡   
ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስን የማቋረጥ ተግባር ድርጊቱን ከሚፈጽሙት ሴቶች አካላዊና ስነል ቡናዊ ጤንነት መቃወስ ባሸገር ከፍተኛ ወጪን የሚያስከትል መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት በገጹ አሳይቶአል፡፡ ይህ ወጪ በተለይም ሕክምናውን በማድረጉ ረገድ በታዳጊ አገሮች የህክምና ወጪ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያስከትል መሆኑን ዝግቦአል፡፡
በአለም ላይ ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ጽንስን ያቋረጡ ሴቶች መለስተኛ የሆነ የጤና ችግርን ለመከላከል የተሰጠ ሕክምና አመታዊ ወጪ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
ደህንነቱ ያልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ከተፈጸም በሁዋላ ልጅን መውለድ ከመቻል ጋር በተያያዘ የተሰጠ ሕክምና አመታዊ ወጪ በአለም ላይ 6/ቢሊዮን ዶላር ያህል ነው፡፡
ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በግላቸው ጽንስን ከማቋረጥ በሁዋላ ለሚፈጠሩ የጤና እውክታዎች ለሕክምና እርዳታ በግላቸው በየአመቱ እስከ 200/ሚሊዮን ዶላር
እንደሚያወጡ ታውቆአል፡፡
ደህንነቱ ባልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ሳቢያ ለሚደርሱ የረጅም ጊዜ የአካል መጎዳት፤ ሕመም፤ እንዲሁም ሞት እና በሞት ምክንያት ለሚቋረጠው የገቢ እጦት፤ በግለሰቦች እና አብረዋቸው ባሉ የህብረተሰብ አካላት በየአመቱ የሚተመነው ወጪ እስከ 930/ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል፡፡
ይህን አስከፊ ችግር ለመከላክል የአለም የጤና ድርጅት በተለያዩ ጊዜያት ሀገራት መመሪያቸው አድርገው ዜጎቻቸውን በጤናው አገልግሎት እንዲንከባከቡ የተለያዩ መመሪያዎችን ከ2012-2018 ድረስ ይፋ አድርጎ ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ ወደፊትም ሀገራት የሴቶችን፤ የታዳጊዎችን፤ አካልና ሕይወት ለማትረፍ እሚያስችል ስራ እንዲሰሩና የህክምና ወጪውም እንዲቀንስ ለማ ድረግ በመላው አለም በተለ ይም በታዳጊ ሀገራት ጠንካራ ስራ መሰራት እንዳለበት የአለም የጤና ድርጅት ያሳስባል፡፡


Read 12451 times