Print this page
Saturday, 30 May 2020 13:33

የሌሊሳ ግርማ “ነፀብራቅ” እየመጣ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)

  ለበርካታ ዓመታት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ መጣጥፎችና አጭር ልብወለዶች በማቅረብ የሚታወቀው ደራሲ ሌሊሳ ግርማ “ነፀብራቅ” የተሰኘ ስድስተኛ መፅሐፉን በቅርቡ ለንባብ እንደሚያበቃ አስታወቀ፡፡
“ነፀብራቅ” ከሃምሳ በላይ መጣጥፎችን ማካተቱን የገለፀው ደራሲው፤ መጣጥፎቹ ማህበራዊ ሂስ የሚያሄሱና ፍልስፍና ነክ ጽንሰ ሃሳቦችን የያዙ ናቸው ብሏል፡፡ በ264 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በጃፋርና ሌሎች መፃህፍት መደብሮች እንደሚሰራጭ ታውቋል::
 ደራሲው ከዚህ ቀደም “የንፋስ ህልም እና ሌሎች የምናብ ታሪኮች”፣ “አፍሮጋዳ”፣ “መሬት - አየር - ሰማይ”፣ “የሰከረ እውነታ” እና “እስቲ ሙዚቃ” የተሰኙ መፃሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል፡፡  

Read 17243 times