Saturday, 07 July 2012 11:28

“78ኛ ዓመት አክብሯል፡፡

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ዓለምአቀፍ የሐረር ቀን ነገ በሐረር ኢማም አህመድ ስታዲየም መከበር እንደሚጀምር የሐረሪ ብሔራዊ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የቢሮው ሃላፊ ወይዘሪት ሃሰነት አቡበከር በተለይ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በዋናነነት ነገ የሚከፈተው ዝግጅት እስከ ሐምሌ 24 የሚቆይ ሲሆን አምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጐራባች ክልሎች ማለትም ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ድሬዳዋ ይሳተፉበታል፡፡ የሐረሪ፣ ስልጢ፣ አርጐባ፣ አፋር፣ ኦሮሞ እና ሶማሌ ብሔረሰቦች ባህል ላይ ሲምፖዚየም የሚካሄድ ሲሆን አስራሰባተኛው የክልሎቹ ባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በከተማው ይጀመራል፡፡

ከበዓሉ መጀመር በፊት ባለፈው እሁድ በባህልና ዘመናዊ ውዝዋዜ የሰለጠኑ 36 የኪነት ቡድኖች ተመርቀዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ የተለያዩ ቦታዎች እና ከውጭ ሀገራት የተገኙ የክልሉ ተወላጆች እና ሌሎች እንግዶች ወደ ሐረሪ ተመዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የሕዝብ ትምህርት ቤት እንደሆነ  የሚነገርለት በሐረር የሚገኘው “ጌይ መድረሳ” ትምህርት ቤት የተመሠረተበትን 78ኛ ዓመት አክብሯል፡፡

 

 

 

 

Read 1024 times Last modified on Saturday, 07 July 2012 11:33