Saturday, 07 July 2012 11:28

“የበዓል እንግዶች” ነገ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ፀሐፌ ተውኔት እና ጋዜጠኛ ዘካርያስ ብርሃኑ የፃፈውና አርቲስት ዘውዱ አበጋዝ ያዘጋጀው “የበዓል እንግዶች“ ትያትር ነገ ከሰዓት በኋላ በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ይመረቃል፡፡ ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8፡30 ለተመልካች በሚቀርበው ትያትር ላይ ሃና ተረፈ፣ ተስፋ ብርሃኔ፣ ዮናስ ጌታቸው፣ ትዕግስት ግርማ፣ ሸዊት ከበደ እና አብዱልከሪም ጀማል ይተውኑበታል፡፡ ደራሲው ዘካርያስ ካሁን ቀደም “ዕጣ ፈለግ”ን፣ ጨምሮ “የተረሳው ዕዳ” እና “ናፋቂዎች” የተሰኙ ትያትሮችን ለሕዝብ ያቀረበ ሲሆን  የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤፍ ኤም 98.1 ዋና አዘጋጅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡  ይህ በዚህ እንዳለ በዘነበ ተስፋዬ (ዲንጐ) ተጽፎ አልአዛር ሳሙኤል እና ቅድስት ገብረሥላሴ ያዘጋጁት “ግራና ቀኝ” ቴአትር ትናንት ከሰዓት በኋላ ተመረቀ፡፡ በትያትሩ ላይ ሕሊና ሲሳይ፣ መቅደስ ፀጋው፣ ያሬድ ኤጉ፣ ቅድስት ገብረሥላሴ እና ኤልያስ ደጀኔ ተውነውበታል፡፡

Read 978 times